ወደ ዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ በተለያዩ ስፔሻሊቲ የትምህርት ዘርፍ ትምህርታቸዉን እንዲከታተሉ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጤና ሚኒስተር ለተላኩ ተማሪዎች ገለፃ ተሰጣቸዉ ፡፡
ገለፃዉን የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ቺፍ አካዳሚክ ጉዳዩች ዳይሬክትር ዶ/ር መንግስቱ መስቀሌ፣ ዶ/ር አምደፅዮን የማኔ ህክምና ት/ት ቤት ዲን ፤ ዶ/ር ሽጉጤ ሹኬ ቀዶ ህክምና ት/ት ክፍል ኃላፊ እንዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በጋራ ሰጥቷል፡፡
ዶ/ር መንግስቱ መስቀሌ የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ቺፍ አካዳሚክ ጉዳዩች ዳይሬክትር ፣ ኮሌጁ በመማር-ማስተማር ፣ በምርምር ፣ማሕበረሰብ አቀፍ አገልግሎት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በጤናዉ ዘርፍ በሽታን በመከላከል ፣ አክሞ በማዳንና የማገገሚያ አገልግሎት በመስጠት በ2022 ዓ.ም የኩላሊትና የካንሰር የልህቀት ማዕከል ለመሆን በትኩረት እየሰራ ያለ ተቋም መሆኑን ለተሳታፊዎች አብራርተዋል፡፡
ዶ/ር መንግስቱ አክለዉ፤ ሆስፒታሉ ከተቋቋመበት 1920 ዓ.ም ጀምሮ ለበርካታ ዓመታት በመጀመሪያ ደረጃ ፣ በጠቅላላ ሆስፒታል ደረጃ እንዲሁም በአሁን ሰዓት በኮምፕርሄንስቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ደረጃ ከፍ ብሎ ከ15ሚሊዮን በላይ ከወላይታና አጎራባች ዞኖች እንዲሁም ከክልሎች የሚመጡ ታካሚዎችን በቀን በአማካይ 1200 በላይ ህሙማንን በተሟላ ዘመናዊ የምርመራ ማሽኖች በመታገዝ በሙያቸዉና በሥነ-ምግባራቸዉ አንቱ በተባሉ ስፔሻሊስት ሀኪሞችንና ጤና ባለሙያዎችን አደራጅቶ ህክምና እየሰጠ ያለ ተቋም ስለመጣችሁ ዕድለኞች በመሆናች ብዙ ዕዉቀትና ልምድ ታገኛላችሁ ብለዋል ፡፡
ስፔሻሊቲ ተማሪዎች ወደ አራት የስፔሻሊቲ ትምህርት ማለትም ቀዶ ህክምና ፣ የዉስጥ ደዌ ህክምና ፣ ህጻናት ህክምና እና ማህጸንና ጽንስ ህክምና ክፍል የመጡ መሆናቸዉን ዶ/ር አምደፅዮን የማኔ ህክምና ት/ት ቤት ዲን ተናግሯ፡፡
ዶ/ር አምደፅዮን የማኔ ፤ ዶ/ር ሽጉጤ ሹኬ ቀዶ ህክምና ት/ት ክፍል ኃላፊ እንዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ለተማሪዎች ለትምህርታቸዉ ዉጤታማነት ገንቢ ሀሳብና ምክር ሰጥተዉ፤ በቀጣይ በየትምህርት ክፍላቸዉ ተመሳሳይ ገለጻ እንደሚኖር አሳስበዋል።
የኮሌጁ ሬጅስተራርና አልሙናይ ዳይሬክተር መ/ር ተክሉ ማረማ በበኩላቸዉ ለተማሪዎቹ ስለምዝገባ ሁኔታ ፣ ት/ት ማስረጃ እንዲሁም አካዳሚክ መርሃ ግብር በተመለከተ አብራርተዋል ሲል የኮሌጁ ኮ/ህ/ግንኙነት ያደረሰን መረጃ ያመለክታል።
