የአንድነትና የሰላም ጥሪ🇪🇹🇪🇹
በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ሰሞኑን እንዲሁም በየወቅቱ ከሰብአዊነት ባፈነገጠ መንገድ በአማራ፣ በዎላይታ እንዲሁም በሌሎች ህዝቦች ላይ ዘርንና ሀይማኖትን መሠረት አድርጎ የምደርሰውን የትኛውንም ጥቃት WT እያወገዘ ለሞቱና ለተጎዱ ወገኖቻችን መፅናናትን ይመኛል።
በመቻቻል፣ በስምምነት እንዲሁም በጋራ መስዋዕትነት የቆመችው ሀገራችን ኢትዮጵያ በልጽጋ ሰላሟ ተረጋግጦ ለሁሉም ዜጎች እኩል ለማድረግ በሚደረገው ጥረት በተላይም መንግስት የህግ የበላይነት በማስከበር፣ ብሄራዊ እርቅ በማድረግ፣ የልዩነት ሀሳቦችን ወደ ሰላማዊ መድረክ በማምጣት የአንበሳውን ድርሻ መውሰድ አለበት እያልን ሁሉም ዜጎች ደግሞ ለስኬቱ ተባባሪ እንዲሆኑ ለጋራ አላማ ደማቸውን ባፈሰሱ አጥንታቸውን በከሰከሱ አባቶቻችንና እናቶቻችን ስም WT ጥሪ ያቀርባል።
ሰላም ለሀገራችን 🇪🇹🇪🇹
