የዎላይታ ሶዶ ከተማ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ከተሞች በአፈፃፀም አንደኛ ሆና ዋንጫ ተሸለመች
የዎላይታ ሶዶ ከተማ በአለም አለም ባንክ (UIIDP) ድጋፍ በኢትዮጵያ በከተሞች ዘርፈብዙ እድገት ላይ በሚያሰሩ ሥራዎች ላይ ከ117 ከተሞች ጋር ተወዳድሮ በአዲስአበባ የኮንስትራክሽን ሚንስትርና ድርጅቱ ባካሄደው በአፈፃፀም ግምገማ አንደኛ በመውጣቱ የዋንጫ እና የተጨማሪ በጀት ተሸላሚ መሆኑን ከፅ/ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያለመለክታል።
ከተማዋ በኢትዮጵያ በአለም ባንክ ከሚደግፉ 117 ከተሞች መካከል በ2ኛው አመታዊ የድርጅቱ በመገምገምያ መስፈርት 99.2 % በማስመዝገብ የዋንጫና ተጨማሪ የበጀት ድጋፍ አግኝቷል።
የአለም ባንክ ለዎላይታ ሶዶ ከተማ ለዘንድሮው በጀት አመት ብቻ ከ160 ሚልዮን በላይ አፅድቆ ወደ ስራ መገባቱንም ለማውቅ ችለናል።
ከዎላይታ ሶዶ ከተማ በተጨማሪ በዞኑ የአረካ ከተማ እና ቦዲቲ ከተማ የዚሁ የUIIDP ፕሮጀክት ተጠቃሚ ናቸው።
