sfdg

ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ተጠናቀቀ

በክልሉ ምክር ቤት ሲካሄድ የነበረው የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ በማጽደቅ ተጠናቋል።

ጉባኤውም የክልሉን ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ረቂቅ ቃለ ጉባኤ ማጽደቅን ጨምሮ የክልሉን መንግስት የ2014 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ሪፖርት አድምጦ በስፋት በመወያዬት አጽድቋል።በተያያዘም በክቡር ርዕሰ መስተዳድር የቀረበለትን የምክር ቤቱን ምክትል አፈ ጉባኤና የክልሉን የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሹመቶችን ተቀብሎ አጽድቋል።

ለምክር ቤቱ በተሰጠው ውክልና መሠረት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና የቋሚ ኮሚቴ አባላት መልምሎ ስራ እያሰራ መቆየቱን የጠቆሙት የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፋጤ ምክር ቤቱም የቀረበለትን የቋሚ ኮሚቴዎች ሹመት ተቀብሎ እንድያፀድቅ ጠይቀዋል። በዚህም መሠረት በምክር ቤቱ የተደራጁ የአምስት ቀሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችን ሹመት ምክር ቤቱ ተቀብሎ አጽድቋል።

ሌላው የትምህርት ኮሌጆች አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 193/2014 ዓ.ም ሆኖ በሙሉ ድምፅ ጸድቋል። በመጨረሻም የ2014 በጀት ዓመት ተጨማሪ በጀት ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 194/2014 ሆኖ ብር 697,087,375 (ስድስት መቶ ዘጠና ሰባት ሚሊዮን ሰማኒያ ሰባት ሺህ ሶስት ሰባ አምስትብር) በማጽደቅ ጉባኤው ተጠናቋል።