ot-1

የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በህግ ማስከበር ዘመቻ ላበረከተው አስተዋጽኦ የዋንጫ እና የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበረከተለት።

ሆስፒታሉ በኢትዮጵያ በተደረገ የሕግ ማስከበር ዘመቻ፤ የሕብረ ብሔራዊ አንድነት ዘመቻ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የተቀናጀ የሕክምና አገልግሎት በመስጠት ሕይወትን የመታደግ እና የኃይል አባዥነት ሚናን በማበርከት በተፈጸመ ሙያዊ አስተዋጽኦ ሽልማቱ እንደተበረከተ ተጠቁሟል።

በተያያዘ ዜና፤ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በፌዴራል ጤና ሚኒስቴር በተደረገ አጠቃላይ የአፈጻጸም ግምገማ ተፈላጊውን ሙያዊ ፥ ድርጅታዊ እና ሌሎች መስፈርቶችን ማሟላቱ ተረጋግጦ በዛሬው ዕለት የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት እንደተበረከተለት ይታወቃል።