
ከትናንት ወዲያ አከባቢ ይህ የሆነው በደቡብ ክልል ጌዴዮ ዞን ዲላ ዙሪያ ጪጩ ጤና ጣቢያ ነው።
ነገሩ እንዲህ ነው፥ በአልጋው ላይ ያለችው ወላድ ስምረት ጥላሁን ትባላለች ። ባሳለፍነው ሳምንት በቤቷ ውስጥ ሆና ምጧ ይመጣና ቤተሰቦቿ አንቡላንስ ጠርተው አከባቢው ላይ ወዳለ ጤና ጣቢያ ይወስዷታል። በሰላም ተገላገለች ከዚያ በኋላ ነው እንግዲህ በምታዩት ሁኔታ መፀዳጃ ቤት ውስጥ ያሳረፏት!!
በጣም የሚያሳዝነው ወላዷ ማዬት የተሳናት በመሆኗ ወዴት እንዳስገቧት አላወቀችም ነበርና ያለችበት ቦታ ጠረኑ ሲያውካት ምንድነው ብላ ቤተሰቦቿን ትጠይቃለች። እነሱም “ቦታው ቆሻሻ ስለሆነ ነው” ከማለት ወጪ ያብራሩላት ነገር አልነበረም። ቤተሰቦቿ ይህን ያደረጉት ያለችበት ቦታ መፀዳጃ መሆኑን በመግለፅ የሞራልና የስነ ልቦና ጉዳት እንዳይደርስባት በማሰብ ነበር።
የወላዷ እህት በስልክ እንደገለፀችልኝ ከሆነ እንዴት እንዲህ አይነት ነውር ትሰራላችሁ በማለት ለጤና ጣቢያው ሃላፊዎች ጥያቄ ብታቀርብም ከሃላፊዎቹ ያገኘችው ምላሽ ዛቻና ማረስፈራሪያ ብቻ ነበር ተብሎ ነበር
ያንን ተከትሎ ጉዳዩን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሃዋሳ ቅ/ፅ/ቤት መረጃው ትክክል መሆኑንና ድርግቱ መፈፀሙን ክትትል በማድረግ አጣርተው አረጋግጧል።
ይህን ድርግት የፈፀሙ የጤና ጣቢው ሰራተኞች ሃላፊዎች በህግ እንዲጠየቁ ብዙ የተሄደበት ሲሆን ጉዳዩን የጌዲኦ ዞን አስተዳደር የጌዲኦ ዞን ፖሊስ መምሪያ ጋርም እንደደረሰና እንደተነጋገሩ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሃዋሳ ቅ/ፅ/ቤት ም/ኮሚሽነር አቶ ኤፍሬም ፋልታ ሃይራ በስልክ አሁን አውርተውኛል::
ይሁን እንጂ የጤና ጣቢው ሰዎች መረጃውን ለማፈን በጣም ብዙ ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
ዛሬ ጥዋት የወላዷን ቤት ሲፈልጉ እንደነበረ የወላዷ እህት ገልፃልኛለች ።
ይህ እንዲህ እንዳለ ቀን 6:0 ሰዓት አከባቢ ከዞኑ መንግሥት ኮሚኒኬሽን ቢሮ የሄዱ ሰዎች ይቅርታ እንዲያደርጉላቸውና ገንዘብ እንደሚሰጧቸው አውርተው ነበር ::
ይሁንና የጉዳቱ ሰለባ የሆኑት ቤተሰቡ በሙሉ ገንዘቡን አንቀበልም ፍትህ ነው የምንፈልገው ብለው እንደመለሷቸው ከሰዓታት በፊት በስልክ አውርተውኛል።
እንዲሁም የፌዴራል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ መረጃው ደርሷቸዋል ነገር ግን ዛሬ እሁድ ስለሆነ ምላሻቸውን ለማግኘት አልተቻለም ተብሏል ስትል ጋዜጠኛ ትዕግስት ታንቱ ገልፃለች።