fb_img_16478785666831801912377389407659

የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከዩኒቨርሲቲው ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጋር በመተባበር ለተቋሙ ሠራተኞች የምስጋና ፕሮግራም አካሄዱ።

“ከፍ ብለን እንደ ንስር በመብረር የተቋማችንን ሁለንተናዊ ለውጥ እውን ለማድረግ በትጋት መስራት ከሁላችን ይጠበቃል” ሲሉ በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ታከለ ታደሰ ተናግረዋል።

ከሰሞኑን የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በፌዴራል ጤና ሚኒስቴር በተደረገ አጠቃላይ የአፈጻጸም ግምገማ ተፈላጊውን ሙያዊ ፥ ድርጅታዊ እና ሌሎች መስፈርቶችን ማሟላቱ ተረጋግጦ በዛሬው እለት የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት እንደተበረከተለት ይታወሳል።

በተጨማሪም በኢትዮጵያ በተደረገ የሕግ ማስከበር ዘመቻ፤ የሕብረ ብሔራዊ አንድነት ዘመቻ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የተቀናጀ የሕክምና አገልግሎት በመስጠት ሕይወትን የመታደግ እና የኃይል አባዥነት ሚናን በማበርከት በፈጸመው ሙያዊ አስተዋጽኦ ለሆስፒታሉ ሽልማቱ እንደተበረከተ ይታወቃል።

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከዩኒቨርሲቲው ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጋር በመተባበር በጋራ ለተገኘው ስኬት የምስጋና ፕሮግራም በማዘጋጀት ሰራተኞችን አመስግኗል።

በስነስርዓቱ ላይ የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳ ት ፕ/ር ታከለ ታደሰ፣ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብርሃም ቦሻ፣ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስክዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ሉቃስ ዲንጋቶን ጨምሮ ሌሎች የማኔጅመንት አባላት ትገኝዋል።

በመርሃግብሩ ላይ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፤ ተቋሙ የወላይታና አጎራባች አካባቢዎች በስፋት የሚገለግሉበት መሆኑን ጠቁመው፤ በተቋሙ የሚገኙ ሠራተኞች ሳይታክቱ ያስመዘገቡትን ውጤት በቀጣይም አጠናክረው እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ዶ/ር ሉቃስ አክለውም የሆስፒታሉ ሰራተኞ በዘመቻው ለተጎዱ ዜጎች ሙያዊ የሕክምና አገልግሎት በመስጠት ላበረበቱት አስተዋጽ ይህ እውቅና ለሎች መሰል ስራዎች የሚያነሳሳ እንደሆነ ገልጸው፤ ሆስፒታሉ በፌዴራል ጤና ሚኒስቴር በተደረገ ግምገማ ተፈላጊውን መስፈርቶችን በማሟላት እውቅና እንዲያገኝ መላው የተቋሙ ሰራተኞች ላበረከቱት አስተዋጽኦም አመስግነዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ታከለ ታደሰ፤ ከፍ ብለን እንደ ንስር በመብረር የተቋማችንን ሁለንተናዊ ለውጥ እውን ለማድረግ በትጋት መስራት ከሁላችን ይጠበቃል ብለዋል።

ተቋሙ በአጭር ጊዜ የለውጥ ጉዞ ውስጥ ገብቷል፤ ይህን የለውጥ ኃይል አቀናጅቶ በመምራት የበለጠ ውጤት ማስመዝገባችን በተቀናጀ መልኩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።

የሕክምና አገልግሎቱን ይበልጥ ለማዘመን የሕክምና ተቋማት ግንባታ እና ግብዓት የማሟላት ተግባር ላይ በስፋት ይሰራልም ብለዋል ፕ/ር ታከለ ታደሰ።

መልካም አስተዳደርን በማስፈን ሁለንተናዊ ለውጥን ለማምጣት አመራሩ ከባለሙያው ጋር ተቀናጅቶ በመስራት አለበት ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ተቋሙ ያስመዘገበው ውጤት በቀጣይም የበለጠ ቅንጅታዊ አሰራርን በማስፈን ተጠናክሮ እንዲቀጥል የጋራ ርብርብ እናድርግ ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመድረኩ የኮሌጁ እና የሆስፒታሉ የ2014 የግማሽ ዓመት የፋይናንስ አፈጻጸም ሪፖርት በዩኒቨርሲቲው የፋይናንስና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ተክሉ መና ቀርቦ ሰፊ ውይይት መደረጉን የዩንቨርስቲው ኮሙኒኬሽን ዳይሮክቶሬት ያደረሰን መረጃ ያመለክታል።
wolaitatimes.com