
የዎላይታ ዞን የመንግስት ስራ ኃላፊዎች በዳሞት ፑላሳ ወረዳ በመገኘት የበልግ ልማት ሥራዎች ያሉበት ደረጃ መስክ ምልከታ አደረጉ
በዳሞት ፑላሳ ወረዳ የበልግ ልማት ሥራዎች ያሉበት ደረጃ የዞንና የወረዳ አስተባባሪ አካላት በተገኙበት የመስክ ምልከታ ተደርጓል።
በመስክ ምልከታው ላይ የተከበሩ የዎለይታ ዞን ም/አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አድማሱ አወቀ፣ የዞኑ ፖለቲካና ርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ፎላ እና የወረዳ አስተባባሪ አካላት ተገኝተዋል።

አሁን ላይ በበልግ ልማት እየለሙ ያሉ የበልግ ልማት ስራ በአርሶ አደር፣ በተቋም እና በሰራ እድል ፈጠራ ደረጃ እየለሙ ያሉ ሰብሎች ያሉበት ደረጃ ተመልክተዋል።
በመስክ ምልከታው ለአርሶ አደሩ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍና ክትትል እደሚያደርጉ ገልጽዋል።