
የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ ሕዝባዊ ውይይት ለማድረግ ጋሞ ዞን መዲና አርባምንጭ ገቡ።
ለእንግዶች የጋሞ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ እና የዞኑ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በአርባምንጭ ኤርፖርት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የብልጽግና ፓርቲ በቅርቡ ባካሄደው የመጀመሪያ ጉባኤው በመከረባቸው ውሳኔዎችና አቋሞች ላይ የጋራ መግባባት የሚፈጥሩ እንዲሁም የጉባኤው ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎችን የሚያጎለብቱ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፉበት የውይይት መድረክ ነገ በአርባምንጭ ከተማ ይካሄዳል ሲል የዞኑ ኮሙኒኬሽን መምሪያ ዘግቧል።
wolaitatimes.com