16479448559913457888632603019843

ቻይና ከትላንናው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ እስካሁን አንድም የተረፈ ሰው አልተገኘም ብላለች።

ትናንት 132 ሰዎች አስፍርኖ የነበረ ” ቦይንግ 737-800 ” አውሮፕላን በቻይና ምስራቃዊ ክፍል በደቡባዊ ጓንጊዢ ተራራማ ቦታ ላይ መከስከሱ ይታወሳል።

ምባልባት ከአደጋው የተረፈ ሰው ይኖር እንደሆነ በነፍስ አድን ሰራተኞች ፍለጋ ቢደረግም እስካሁን በህይወት የተረፈ ሰው ማግኘት አለመቻሉን የቻይና መንግስት አስታውቋል፡፡

የነፍስ አድን ሰራተኞች ከአውሮፕላን መከስከስ አደጋው በህይወት ያለ ሰው የማግኘት ተስፋቸው መደብዘዙን ማሳወቃቸውን TRT ዘግቧል።