16479640116376346639206501303532

በዎላይታ ዞን በሁሉም አካባቢዎች የህዝብ ተወካዮችና የክልል ም/ቤት አባላት በየደረጃው ከህዝቡ ጋር በተካሄዱት መድረክ የተነሱ ጥያቄዎች ዙሪያ ከአስፈጻሚ ባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡

በየአከባቢው ህዝቡ ያነሳቸው የተለያዩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በዞን ደረጃ ምለሽ የሚያስፈልጋቸውን የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባልና የልዑካን ሰብሳቢ አቶ መለሰ መና አቅርበዋል፡፡

የልማት፣ የመልካም አስተዳደር፣ የስራ አጥት ችግር፣ የኑሮ ውድነት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የሠላምና ፀጥታ፣ የበጀት እጥረት፣ ፍታሃዊ ሀብት ተጠቃሚነት እና መንግስት ለህዝቡ ቃል የገባቸው ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ህዝቡ በየመድረኩ ያነሳቸው ጥያቄዎች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ 

የመምህራን ደረጃ ዕድገት፣ የጤና ባለሙያዎች ዱት፤ የውዝፍ JEG ክፍያና ደመወዝ በወቅቱ ያለመከፈል ችግሮች ከመንግስት ሠራተኞች ዘንድ የሚነሱ ጥያቄዎች መሆናቸውንም አስታወቀዋል፡፡ 

ህዝቡ ያነሳቸው ጥያቄዎች በአግባቡ ተለይተው አስፈጻሚ አካላት ህዝቡ እርካታ እንዲያገኝ በቀርበት በመናበብና በመቀናጀት ለመመለስ መረባረብ እንዳለባቸው አቶ መለሰ አሳስበዋል፡፡

ህዝቡ አገልግሎቱን ለማግኘት በገንዘብ የሆነበት ጊዜ ላይ ደርሰናል ብለዋል ያሉት አቶ መለሰ በተላይም በማዘጋጀ ቤቶች አንጻር ህብረተሰቡን የሚያማሪሩ ጉዳዮችን ለማረምና ፍታሃዊ አገልግሎት እንዲያገኙ ሰር ነቀለ ለውጥ ማምጣት ያፈልጋል ብለዋል፡፡

ክትትልና ቁጥጥር አንዱና ዋናው የምክር ቤቱ ሥራ መሆኑን የገለጹት አቶ መለሰ የታቀዱ ዕቅዶች ስለመፈፀማቸው፣ በህዝብ ላይ የሚታይ ለውጥ ያመጡና የህዝብን ሕይወት የቀየሩ ስለመሆናቸው የበኩላችን መውጣት አለብን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ በበኩላቸው የተነሱት ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በየደረጃው ያለው አመራሮችና ባለሙያዎች የህዝቡን ጥቅም ለማረጋገጥና በተጨባጭ ለውጥን ለማምጣት መረባረብ እንደሚያስፈልግ ዋና አስተዳዳሪው አሳስበዋል፡፡  

ያለንበት አገራዊና ዓለማቀፋዊ ሁኔታዎች ላጋጠሙን ችግሮች በተለይም ለዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት የራሳቸው ሚና ነበራቸው ያሉት አስተዳዳሪው ሰው ሠራሽ የዋጋ ንረት ከመቆጣጠር ባሻገር በእጃችን ያለው መፍትሔ የግብርና ሥራችን አጠናክሮ በመሥራት የምርት አቅርቦት ማሻሻል ነው ብለዋል።

በህዝባችን ዘንድ ያሉ የመልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ከፍ ያሉ መሆናቸውን ተናግረው ህዝቡ የመረጠንና ዕድል የሰጠን ስለሠራን ሳይሆን “ትሠራላችሁ” በሚል ተስፋ ነው በማለት ህዝቡን የሚያማርሩ ችግሮችን በቅደመ ተከተል መፍታትና መካስ አለብን ሲሉ አሳስበዋል።

ከህዝቡ የተነሱ ጥያቄዎችን ከፌደራል አስከ ቀበሌ ድረስ በየደረጃው ያሉ ተቋማት ችግሮቹን ለመፍታት ድርሻቸውን እንዲወጡና ህዝቡም የበኩለን ሚና ልወጡ በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ሰፊ  ውይይት በማድረግ መግባባት ተደርሶ መድረኩ ተጠናቅቋል፡፡

በውይይት መድረኩ የህዝብ ተወካዮችና የክልል ም/ቤት ተመራጮች፣ የዞኑ አጠቃላይ  አመራር፣ የፍትህ ተቋማት ኃላፊዎችና ሌሎች አስፈጻሚ አካላት መገኘታቸውን ከዞኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።