
የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ በበኩላቸው በሀገራዊ ጉዳዮችና በተለያዩ ምክንያት ሳይመለስ የቆየው የዎላይታ ክልል አደረጃጀት ጥያቄ ህግና ሥራዓቱን ተከትለው መንግስት ይፈጸማል ብለዋል፡፡
የሥራ አጥነት ችግርን ትርጉም ሰጥተው ለመፍታት ብልጽግና ፓርቲ ጉባኤው ከወሰነው ውሳኔዎች ዋነኛውና ቀዳሚ መሆኑን ዋና አስተዳዳሪው ጠቅሰው ለዚህም ሁሉም ድርሻውን ወስደው መረባረብ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
በዎላይታ ልማት ማህበር አማካይኝነት በሶዶ ከተማ ላይ ተጀምረው የቆሙ የታዋቂ ግለሰቦች ሐውልቶች በበጀት እጥርት ምክንያት መሆኑን ያሰረዱት ዋና አስተዳዳሪው ለከተማው ውበት የሚሰጡ ስለሆነ በጀት ተመቻችቶ ሥራው እንደሚጀመሪም አስታውቀዋል፡፡

የህገ-ወጥነትን፣ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ ልብነትና ሙስናን ለመታገል ህዝቡ አንድ ሆነው ግለሰቦችን ለህግ ጥቆማ መስጠት እንዳለበትና ከመንግስት ጎን መቆም እንዳለባቸውም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የትርጉም አፕሊኬሽን ለሰዎች በቀላሉ እንዲደርስ automatically የሚቀየር ነው አንጂ ዜናዎቻችን በአማርኛ ብቻ እየፃፍን ነው። ወደፊት የሰው ሀይል ስሟላና አቅም ስናገኝ አንተ ያልከውን ተግባራዊ እናደርጋለን። እናመሰግናለን።
Use either proper English or stop reporting in English. It is terribly below standard and lacks basic grammar knowledge