
ከህብረተሰቡ የሚነሱ የተለያዩ ጥያቄዎችን ለመመለስ በመመካከር፣ በመነጋገርና በመወያየት የጋራ አቋምና አቅጣጫ መያዝ እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ
የብልጽግና ፓርቲ 1ኛ ታሪካዊ ጉባኤ ያስቀመጠውን አቅጣጫዎችንና የወሰናቸውን ውሳኔዎችን መሠረት ያደረገ የህዝብ መድረክ ተጠናቀቀ፡፡
የክልል አደረጃጀት፣ የመሠረተ-ልማት፣ የመልካም አስተዳደር፣ የስራ አጥነት ችግር፣ የኑሮ ውድነት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ጉድለት፣ የሠላምና ፀጥታ፣ የበጀት ዉስንነት፣ የኢንዳስትር ፓርክ እና መንግስት ለህዝቡ ቃል የገባቸው ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ የመደረኩ ተሳታፊዎች ጠይቀዋል፡፡
ከህብረተሰቡ የተነሱ አንገብጋቢ ጥያቄዎችን መደረኩን የመሩት የፌደራል፣ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
የኢፌዴሪ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ህዝቡ ከጠየቁት ጥያቄዎች መካከል የኢንዳስትር ፓርክ በአካባበው ፀጋና አቅርቦት እንድሁም አዋጭነትን መነሻ ተድርጎ ታቅዶና ተወያይተው እንደሚታይ ተናግረዋል፡፡
ዘላቂ ሰላምን ለማምጣትና ለማረጋገጥ በመመካከር፣ በመነጋገርና በመወያየት የጋራ አቋምና አቅጣጫ መያዝ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
አሁን የምንተኛበት ጊዜ ላይ አይደደለም÷ ታታር መሆን አለብን ያሉት አቶ ተመስገን ለሁሉም ጥያቄዎች መፍተሔው እኛው ነን ብለዋል፡፡

የደቡብ ክልል የገቢዎች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ዘይቱና ኢብራሂም የኑሮ ወድነት ለመቅረፍ ከፍተኛ የደላላ ስንሰለት መበጠስ እንዳለበትና ሁሉም ህብረተሰብ ክፍሎች የግብርና ሥራዎችን በማዘመን የቻለውን ማመረት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ከኢንቨሲትመንት ጥያቆች ምላሽ ያላገኙትን የክልሉ ካቢኔ አባላት ተወያየተው በአጭር ጊዜ ውሳኔ ይሰጣል ያሉት ወ/ሮ ዘይቱና ኢንቨስትመንት የተሰማሩ ባለሀብቶች በአግባቡ ወደ ሥራ ቢገቡ በክፍል የሥራ አጥነት ችግር ልቀረፍ ይችላልም ብለዋል፡፡
የመሠረት ልማት ጥያቆችን በአግባቡ መመለስ የሚችለው የገቢ አመራጮችን አሟጥጦ መሰባሰብ ስንችል ብቻ እንደሆን ጠቁመዋል፡፡
የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ በበኩላቸው በሀገራዊ ጉዳዮችና በተለያዩ ምክንያት ሳይመለስ የቆየው የወላይታ ክልል አደረጃጀት ጥያቄ ህግና ሥራዓቱን ተከትለው መንግስት ይፈጸማል ብለዋል፡፡
የሥራ አጥነት ችግርን ትርጉም ሰጥተው ለመፍታት ብልጽግና ፓርቲ ጉባኤው ከወሰነው ውሳኔዎች ዋነኛውና ቀዳሚ መሆኑን ዋና አስተዳዳሪው ጠቅሰው ለዚህም ሁሉም ድርሻውን ወስደው መረባረብ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

በወላይታ ልማት ማህበር አማካይኝነት በሶዶ ከተማ ላይ ተጀምረው የቆሙ የታዋቂ ግለሰቦች ሐውልቶች በበጀት እጥርት ምክንያት መሆኑን ያሰረዱት ዋና አስተዳዳሪው ለከተማው ውበት የሚሰጡ ስለሆነ በጀት ተመቻችቶ ሥራው እንደሚጀመሪም አስታውቀዋል፡፡
የህገ-ወጥነትን፣ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ ልብነትና ሙስናን ለመታገል ህዝቡ አንድ ሆነው ግለሰቦችን ለህግ ጥቆማ መስጠት እንዳለበትና ከመንግስት ጎን መቆም እንዳለባቸውም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ከሌዊ እስከ ግብርና ኮሌጅ የሚወስደው አስፋልት መንገድ ከሶስት ዓመታት በፍት ዲዛይን ማለቁን የሶዶ ከተማ ከንቲባ አቶ መርክኔ ማለዳ ገልጸው አሁን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተናጋግረን በሂደት ላይ እንደሚገኝም መገለፁን ከዞኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
nonesense conference as usual . Wolaitans demanded their self-determination which is mandatory for survival. No need of going other way around. Discussion is not needed with regarding regional state quest of Wolaita . Already done by people. Constitution and people must be respected. PP has been doing more than enough illegal practice