የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰብኣዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑን በበጎ እንደሚቀበለው አስታውቋል።

በኢትዮጵያ የሚገኘው የብሪታኒያ ኢምባሲ በላከው መልእክት እንዳስታወቀው ኢትዮጵያ ዓለም ዐቀፍ ለጋሾች የሰብኣዊ ድጋፍ ወደ ትግራይ እንዲያስገቡ በመፍቀዷ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጎን እንደሚቆም ገልጿል። 
 
የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥትም በኢትዮጵያ በኩል የተወሰደውን እርምጃ ተከትሎ ለአገሪቱ የሚያደርገውን ሰብኣዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል።

ዓለም ዐቀፉ የለጋሾች ማኅበረሰብ እያቀረበ ያለውን ድጋፍ እና እርዳታ በከፍተኛ መጠን እንዲጨምር የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ቀደም ሲል ባወጣው መግለጫ ጥሪ አቅርቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: