hqgfgsdf

የኢፌዴሪ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ጨምሮ ሌሎች የክልልና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች በዎላይታ ዞን የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ጎበኙ

የኢፌዴሪ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ጨምሮ ሌሎች የክልልና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች በወላይታ ዞን ከህዝቡ ውይይት መድረክ ምልስ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ተዘዋዉረው ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸው በቁጭት ተጀምሮ ለከፍተኛ ውጤት የበቃውን የበጋ መስኖ ስንዴ ምርት ጨምሮ የተለያዩ ሰብሎችን ተመልክተዋል።

በዞኑ የተሰሩ የልማት ሥራዎች ተስፋ ሰጪ መሆኑን አቶ ተመስገን ጠቅሰው ቀጣይ መሻሻል ያሉባቸው ጉዳዮች ታርመው የህዝቡ ጥቅምን ለማረጋገጥ ተጠናክሮ መሠራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡  መንግስት በሀገር አቀፍ ደረጃ በቁጭት ያስጀመረው የበጋ መስኖ ስንዴ ለውጤት መብቃቱን በማየት መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡

ለቀጣይም ከዚህ በበለጠ ይህ የተጀመረው ምርጥ ተሞክሮ ለአካባቢው ሆነ ለሌሎች ማህበረሰብ ክፍሎች መስፋፋት እንዳለበት አስተያየት ሰጥተዋል።

መንግስት ባመቻቸው ዕድል ተጠቅመው በአከባቢው በኢንቨስትመንት ሥራ ላይ የተሰማሩ የግል ባለሀብቶች በከፍተኛ ወኔ የጀመሩትን ሥራ ለወደፊትም አጠናክሮ መቀጠል እንዳለባቸው አስታውቀዋል።