ድንበር ዘልቀው የገቡ የኬንያ ቱርካና ታጣቂዎች በኢትዮጵያ ዳሰነች ወረዳ ባደረሱት ጥቃት የሰው ህይወት መጥፋትና የንብረት ዘረፋ መድረሱን የወረዳው አስተዳደር ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያን ድንበር ዘልቀው የገቡ የኬንያ ቱርካና ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የ4 ሰው ህይወት ሲያልፍ በሦስት ሰው ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

በትናንትናው ዕለት በቀን 18/07/2014 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡00 አከባቢ የኢትዮጵያን ድንበር ዘልቀው የገቡ የኬንያ ቱርካና ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ህይወታቸው አልፏል፡፡

በሁለቱ ሀገራት የድንበር አከባቢዎች በሚከሰት ግጭት የሚደርስን ሞትና የንብረት ውድመትን ለመከላክለና  እና ለመቆጣጠር እንዲሁም ግጭቶችን በዘላቂነት ለማስቀረት የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት በልዩ ትኩረት ሊሰሩ ይገባል ሲሉ የዳሰነች ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅረማሪያም አይመላ ማሳሰቡን ከወረደው ኮሙኒኬሽን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *