FB_IMG_1648721782622

አሜሪካ የኢኮኖሚ እና ንግድ ጉዳዮችን ለፖለቲካ ፍጆታ ከማዋል እንድትቆጠብ ቻይና ጠየቀች አሜሪካ በቻይና የኢኮኖሚ እና ንግድ ጉዳዮች ላይ ያላትን የተሳሳተ አቀራረብ በአስቸኳይ እንድታርም የቻይና ንግድ ሚኒስቴር አስጠነቀቀ፡፡

የቻይና ንግድ ሚኒስቴር ÷ ቻይና በምታደርጋቸው የንግድ እንቅሥቃሴዎች ላይ ጫና በመፍጠር ኢኮኖሚዋን ለመጉዳት አሜሪካ ፖለቲካዊ ጫና እያሳደረች ነው ሲል ይከሳል፡፡

ሚኒስቴሩ አሜሪካ በቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት እና በመገናኛ ቁሳቁስ ሽያጭ ዘርፍ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ “ቻይና ቴሌኮም አሜሪካስ” እና “ቻይና ሞባይል ኢንተርናሽናል ዩ ኤስ ኤ” የተሰኙትን የቻይና ኩባንያዎች ለብሔራዊ ደኅንነቴ ስጋት ናቸው ብላ መፈረጇን ሚኒስቴሩ ጠቁሟል፡፡

የቻይና ንግድ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሹ ጁቲንግ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ÷ አሜሪካ ኩባንያዎቹን በዚህ መልኩ መፈረጇ ፍጹም ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ገልጸዋል።

ቃል አቀባዩ ቻይና መብቷን ለማስከበርም አስፈላጊውን ሁሉ እርምጃ በቆራጥነት ትወስዳለች ማለታቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።