

ነፃ ሀሳብ ከታሪክ ማህደር
ከዛሬ ስንት ዓመት በፊት እነ ማሀተመ ጋንዲ revolution ከማስነሳታቸዉ በፊት ሂንድ ዉስጥ tribe stratification ነበራቸዉ::ከ higher class(priest)እስከ lower(እነሱ untouchable ይሉታል)::ይህ 1948 በህግ እስከታገድ የቀጠለ ይመስለኛል::ህንድን አነሳሁት እንጂ ይህ የዬሀገራቱ ችግር ነዉ:: አአፍርካ(hunters) እስከ አሜርካ (blacks,red indian) ያለ ችግር ነዉ::በየሀገሩ ቢትሄዱ የራሳቸዉ untouchables out cast አላቸዉ:: ማለትም ማያጋቡ፣ማይቀራረቡ እና አብሮነት የለላቸዉ::እንዲሁም አንዳ’ንድ ማህበረሰብ ሰዉ የመሆን “evolution” ያልጨረሱ ብሎ ያስባሉ::ለዛም ሙሉ የሰዉነት ክብር ይነፍገችዋል:: ሙሉ ሰዉ ናቸዉ ብሎ ለመቀበል ሲደግቱ ይታያሉ::ጽሁፌን ከማንዛዛ የሀሳቤ መነሻ ወደሆነዉ ወደ ሀገራችን አልፎም ወጀ ዎላይታ ላመጣችሁ ነዉ::
ወላይታም እንደ አንድ ትልቅ ማህበረሰብ የችግሩ ተጠቂ ነዉ::ለወላይታም እንደየሀገራቱ ተመሳሳይ የሚመስል የጎሳ ክፍፍል አለዉ:: ከ ንጉስ(Royal family-tigre) እስከ እጅሙያተኞች(cinasha,wogacciya,degela)ድረስ አለዉ::እናም ከእነዚህ ክላሶች ዉስጥ ከ lower class የሆነዉን የሸክላ ሠሪዎች(cinasha) ማህበረሰብ ላሳያችሁ:: አነሳሴ መሉ በሙሉ የእነዚህን ማህበረሰብ historically,economically,polotically እና culturally briefly ለማሳየት ሳይሆን ለሀሳቤ እንዲመች በጨረፍታ አነሳለሁኝ::
ዎላይታ መነሻዉን ከአሩጂያ እስከ አሁኑ ይዞታ ድረስ መሳዊዕት ከፍሎ ዳር ድንበሩን ሲያስከብር እነዚህ ማህበረሰብ የጀርባ አጥንት ሆኖ አልፏል::አይረሰ ታርክም ሰርቷል:: ሴቶች ሸክላ በመሥራት ሲያገለግሉ ወንዶች የሸክላ መሠሪያ አፈር በማቅረብ እና በጦርነትም ተሳትፏል::ለአገልግሎትም ከንጉስ ከምሰጥ ከእጅ መንሻ ማለትም ከዕለት ጉርስ ሌላ አይሰጣቸዉም::ለሌሎች ማለትም ከጨዋ(goqa) ክላስስ ከምባሉት ጦርነት ተዋግቶ ወይንም ጥሩ ነገር ለሀገሩ ለከናወኑት በጎ ተግባር እጅ መንሻ መሬት ይሰጠቿል:: ሌላውም ሌላውም :: ይህ ሁኔታ ለአሁኑ ለእነዚህ ማህበረሰብ የራሱን አሻራ ጥሎ አልፏል:: የዎላይታ ንጉሳዊ ስራዓት ተወግዶ በንጉሡ ሥርዐት ተተክቶ መሻሻያ ቢደረግም እስከ ጃንሆይ ዉድቀት ድረስ የቀጠለ ይመስለኛል::
ትንሽ መሻሻያ ያገኘነዉ ኢጣሊያ ኢትየጵያን በወረረችበት እና በደርግ ጊዜ ነዉ ትላለች አያቴ::የየዛነዉን ሲታወራ አያቴ ፊቷ ፈክቶ ‘ዉይ ደርግ’ ትላለች::አያቴ በዛም ሰዓት የቀበሌ የሴቶች ሊቀመንበር ሆና ሠርታለችና::ይህ ማለት ለእነሱ ምን እንድሆነ የገፈቱ ቀማሽ ያዉቃል::አልፎ ተርፎም እኔ ከእነዚህ ስለሆንኩ በቀጥታ ይሁን በተዘዋዋሪም የገፈቱ ቀማሽ ነኝ::ከምን አይነት ሁኔታ እንዴት እንዳለፍኩ ብቻ ጌታ ይመስገን::አሁን እኛ ከመረትም ከሙያም አልሆነንም:: መሬትን goqa ጎሳዎች ተከፋፍሎ ወሰዷል::ሙያም ቢሆን ደግሞ እንዳለ በ ቻይና ፕላስቲክ ተተክቷል::መተዳደሪያችን ቢያንስ ከ90% ያህል በሸክላ ሥራ ነዉ::ይህንንም እየሠራን ፈጣሪ እስካኖረን ለመኖር ሲንጥር ከህብረተሰቡ የሚደርስ መገለል፣ጥላቻ፣ስድብ እና…ወዘተ ሌላ መከራ ነዉ::በ21ኛዉ ክፍለ ዘመን ሰዉ ሰዉን ይበላል ወይንም ወደ ጅብነት ይቀየራል ብሎ ከሚያስብ የዘቀጠ ትዉልድ ጋር ነን::
አለማችን reasonable እና rational በሆነበት እንዴት ብሎ መጠየቅ::እኛ ግን አሁንም እዛዉ ባለበት ሂድ ላይ ነን::አንድ #Gold Ethiopia በመባል facebook ስም የሚታወቅ ግለሰብ “ያልተወራዉ የሶዶ ችግር ” በሚል ርዕስ ሥር የአንድ ወጣት ታርክ ሠፍሮ ከገጠርቱ ክፍል ወደ ሶዶ ከተማ ፈልሶ ጎዳና ተዳዳሪ የሆኑት ነገር እነዳሳሰበዉና አልፍ ተርፎም ለሀገርና ህዝብ ትልቅ ችግር እንድሆነ አሳስቧል።እዉነቱ ነዉ::ከምፈልሱም አብዛኞቹ ከሸክላ ሠሪ ማህበረሰብ ነዉ::እስቲ ቀረብ ብላችሁ እናት የሆኑትን ነኔ ብጤዎች አናግሩ ትሰሙታላችሁ:: አንዳ’ንዱ #Gold Ethiopia እንደጠቀሰው ወጣት የሥራ አለመዉደድ ቢሆንም የችግሩ አረንቋ የገረፋቸዉም ትንሽ የሚባሉ አይደሉም::
እነዚን ሰዎች እንዴት ከዚህ መዐት እናወጣለን? ለእኔ መፍትሄ የሚመስለኝ:-
1,ከሥሩ ችግሩን መቅረፍ(ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መስጠት(ዋጋ ቢያስከፍልም))
2,መንግስት ከ NGOs ጋር በመተባበር ህብረተሰብን የሚያሳትፍ
3,ልጆቻቸዉን እንዲያስተምሩ ማበረታታት
4,አለፎ ተርፎም psychological ማከም እና የመሳሰሉት ናቸዉ::
እናንተም የራሳችሁን መጨመር ትችላላችሁ:: ይህ ሁሉ እኛም አለን ለማለት ለማስታወስ ነዉ እንጂ ልዩነትን ለማጎላት ወይንም አቃቂር ለማዉጣት አይደለም:: መቼም ቢሆን በወላይታነቴ እኮራለሁ ያስደስታኛልም:: ለፍደል ግድፈት ይቅርታ እጠይቃለሁ:: እግዚአብሔርን ሀገራችን ከክፉ ሀሉ ይሰዉረን!