
ጀልባዋ በሳምንቱ መጨረሻ ከሊቢያ ስደተኞችን ጭና ወደ አውሮፓ ለማሻገር ስትሞክር መስጠሟን አሶሺየትድ ፕረስን ጠቅሶ ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል። አፍሪካውያን ስደተኞች በሜዲትራንያን ባህር ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሊቢያን እንደ መነሻ ይጠቀማሉ። ይሁን እንጅ በዚህ ጉዞ በርካቶች የባህር ሲሳይ ሆነው እንደሚቀሩ መረጃዎች ያመላክታሉ።
ከፈረንጆቹ ጥር 1 እስከ መጋቢት 28 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ 300 የሚጠጉ ስደተኞች በማዕከላዊ ሜዲትራንያን ባህር ሰጥመው ህይወታቸው እንዳለፈ የዓለም አቀፉ ስደተኞች ድርጅት አስታውቋል፡፡ ባለፈው አመትም 1 ሺህ 553 ስደተኞች በዚህ ጉዞ ለህልፈት መዳረጋቸውን ድርጅቱ አስታውሷል።