FB_IMG_1649081948927

በቡራዮ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ምድብ ሐ እየተሳተፈ የሚገኘው አረካ ከነማ እግር ኳስ ቡድን አድስ ከተማ ክ/ከተማ 2-1 በማሸነፍ 1 ቀሪ ጨዋታ እየቀረው የአንደኛ ሊግ ምድብ ሐ የዋንጫ ባሌበት መሆኑን ማረጋገጡን የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ሀብትአብ አለሙ “ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ” ተናግረዋል።

ስለ ቶርናመንት ውድድር በአጭሩ

እንደምታወቀው የኢኢትዮያ 1ኛ ሊግ 3 ምድቦች አሉት ከነዝህ 3 ምድቦች 16 ቡድኖች ይመረጡና ወደ ቶርናመንት ያልፋሉ።

ስንት ቡድን ነው ወደ ቶርናመንት የምያልፋው?

ከምድብ አንድ 6 ቡድኖች

ከምድብ ሁለት 5 ቡድኖች እና

ከምድብ ሶስት 5 ቡድኖች ያልፋሉ

አረካ ከነማ ካለበት ምድብ ሐ ከኛ ምድብ 5 ቡድን እንድያልፍ የተደረገው ከምድብ 1 ግን 6 ቡድኖች እንድያልፉ ይደረጋል ምክንያቱም የተሳታፊ ቁጥር በ1 ይበልጣል ማለት በምድብ 2 እና 3 11 ቡድን ስኖር በምድብ 1 ግን 12 ቡድኖች አሉ።

ወደ ከፍተኛው ሊግ(Super League) ስንት ቡድን ነው የምያልፈው?

6 ቡድን ወደ ከፍተኛ ሊግ ያድጋሉ

ቶርናመንት የሄዱት ቡድኖች በ4 ምድብ ይደለደላሉ ከዛም ከየምድባቸው 2 ቡድኖች ያልፋሉ እኔዛም ያለፉ 8 ቡድኖች እርስበርስ ይጫወቱና የምያሸንፉ 4 ቡድኖች በቀጥታ ወደ ከፍተኛው ሊግ ያልፋሉ
የተሸነፉ 4 ቡድኖች ሌላ ጨዋታ በማድረግ 2ቱ አሸናፍፊ ቡድኖች ወደ ሱፔር ሊጉ ይገባሉ ማለት ነው።

አሁን ላይ አረካ ከነማ አንድ ጨዋታ እያለ ውድድሩን በማሸነፉ ወደ ቶርናመንት መሄዱን አረጋግጧል።