

የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ሊጠናቀቅ የአንድ ሳምንት ጫዋታ ሲቀረው የሶስቱ ምድብ ሻምፕዮና ሙሉ በሙሉ የታወቁ ሲሆን ወደ ቶርናመንቱ (ከፍተኛ ሊግ ለመግባት ) በሚደረገው ውድድር 16 ክለቦች ተሳታፊ የሚሆኑ ሲሆን እስከ አሁን ቦዲቲ ከነማና አረካ ከነማ ጨምረው 11 ክለቦች ያረጋገጡ ሲሆን ቀሪው አምስት ቡድኖች በመጨረሻ ሳምንት ጫዋታ ተለይተው የሚታወቁ ይሆናል።
✅ ከምድብ አንድ (ሀ) በቢሾፍቱ ከተማ በሚከናወነው ጫዋታ አራዳ ክፍለ ከተማ ምድቡን ከተከታዩ ቡሌ ሆራ በአራት ነጥብ በመብለጥ አንድ ቀሪ ጫዋታ እየቀረው የምድቡ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል ።
በዚሁ ምድብ ወደ ማጠቃለያ ውድድር (ቶርናመንት) አምስት ክለቦች ማለፋቸው አረጋግጠዋል።
1. አራዳ ክፍለ ከተማ
2. ቡሌ ሆራ
3. ድሬዳዋ ፖሊስ
4. ዱከም ከተማ
5. ቦዲቲ ከተማ ናቸው።
✅ ከምድብ ሁለት (ለ) በወልቂጤ ከተማ በሚደረገው ውድድር ጅንካ ከተማ ከተከታዩ ሆለታ ከተማ በአራት ነጥቦች በመብለጥ አንድ ቀሪ ጫዋታ እየቀረው የምድቡ አሸናፊ መሆን ችሏል።
በዚሁ ምድብ ወደ ማጠቃለያው ውድድር (ቶርናመንት) ማለፍ የቻሉት ሶስት ክለቦች ሲሆኑ ቀሪዎቹ በመጨረሻ ሳምንት ተለይተው የሚታወቁ ይሆናል።
1. ጅንካ ከተማ
2. ሆለታ ከተማ
3. ሐረር ከተማ ናቸው።
✅ ምድብ ሶስት (ሐ) በቡራዩ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው ምድብ አረካ ከተማ አንድ ቀሪ ጫዋታ እየቀረው ከሌላው ምድብብ በተመሳሳይ ከተከታዩ ሮቤ ከተማ በአራት ነጥብ በልጦ የምድቡ አሸናፊ መሆን ችሏል።
በምድብ ሐ ወደ ማጠቃለያ ውድድር (ቶርናመንት) እስከ አሁን ማለፍ የቻሉት ሶስት ክለቦች ሲሆን ቀሪዎቹ አላፊ የመጨረሻውን ጫዋታ ለመጠበቅ ቸገደዋል።
1. አረካ ከተማ
2. ሮቤ ከተማ
3. አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሲሆኑ ባጠቃላይ ከሶስቱ ምድቦች ወደ ማጠቃለያ ውድድር ማለፍ የቻሉት 11 ቡድኖች ደርሰዋል ቀሪ አምስት ክለቦች የመጨረሻውን ቀሪ ጫዋታ ይጠብቃሉ ስል ዳጉ ስፖርት ዘግቧል።