1649167198610

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የተመራው የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በዳውሮ ዞን ቆላማ አከባቢዎች በተከሰተው ከፍተኛ የምግብ እጥረት ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖቸን ጠየቁ።

ችግሩ በተከሰተበት በዳውሮ ዞን ዛባ ጋዞ ወረዳ በጋራዳ እንታላና በጋራዳ ባጭሪ ቀበሌ ተገኝተው ተጎጂዎችን የጠየቁ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳዳር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋገሾ ከዞንና ከአከባቢው አስተዳደሮች ጋር በመነጋገር ለተከሰተው አስከፍ የምግብ እጥረት ችግር ጊዜያዊ መፍትሄ እየተሰጠ መሆኑን ገልፀው በዘላቂነት ለመቅረፍ በትኩረት እንደሚሰራ ገልፀዋል።

ዝናብ በጊዜ ባለመዝነቡ ምክንያት አከባቢ ምርት እየሰጠ አይደለም ያሉተ ርዕሰ መስተዳድሩ በአከባቢው በተከሰተው የአየር መዛባት መንስኤ በተከሰተው ድርቅ በርካታ ከብቶች እንደሞቱና በርካታ ሰዎች ለምግብ እጥረት እንተጋለጡ አብራርተዋል።

ልዑኩ በዳውሮ ዞን በዛባ ጋዞ ወረዳ በጋራዳ እንታላና በጋራዳ ባጭሪ ቀበሌ በከፍተኛ የምግብ እጥረት ችግር ጉዳት የደረሰባቸውን ተጎጂዎችን ጠይቀዋል።

በልዑካን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳዳር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋገሾን ጨምሮ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው እንዲሁም የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አልማው ዘውዴና ለሎች ከፍተኛ የክልልና የዞን የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል ስል ዘገባው: የዳውሮ ዞን የመን/ኮ/ጉ/መምሪያ ነው።