በኮንሶ ዞን ሠገን ዙሪያ ወረዳ ፅንፈኛው የጥፋት በትሩን በንፁሃን ላይ እያሳረፈ ይገኛል ሲሉ የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ አስታወቀ።

ፀረ ሠላሙ ኃይል ትላንት ምሽት በሠገን ዙሪያ ወረዳ በቾ ቀበሌ ላይ ጥቃት አድርሷል።

በሠገን ዙሪያ ወረዳ ቀበሌያት ላይ ያነጣጠረው የጥፋት ኃይሉ ሴራ በዚሁ ሳምንት በሰገን ገነትና  ገርጨ ቀበሌያት ትላንት ምሽት በቾ ቀበሌያት ላይ በሰው፣ በእንሰሳትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን የዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ሠራዊት ዲባባ አስታውቋል።

በወረዳው የተከሰተውን የፀጥታ ችግር ለማስቆም የክልሉ መንግስት ከፀጥታው መዋቅርና ህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት እየሠራ ባለበት ትላንት ምሽት በበቾ ቀበሌ ቤት ውስጥ ባሉ ሴቶችና ወንዶች ላይ በተከፈተ ተኩስ ከባድና ቀላል ጉዳት ማድረሳቸውና፤ እንሰሳትን ለሞት፣ ቤት ንብረትን ለውድመት ዳርገዋል።

ትላንት ምሽት የበቾ ቀበሌ ከፍተኛ ጉዳት ባስተናገዱበት ማግስት በክልሉ የመንግስት ኮሚኒኬሽን በኩል ሠላም ተፈጥሯል መባሉ የአከባቢውን ህዝብ ቅር አሰኝቷል።

በዞኑና አጎራባች  ሠላም ሰፍኖ ማየት የምጊዜም  ተግባራችን ነው ያሉት መምሪያ ኃላፊው፤ የፀጥታ ችግሮችንና የተኩስ ጥቃት ለማቆም ዞኑ ከክልሉ መንግስት ጋር እየሠራ መሆኑን መምሪያው አስታውቋል።

ከፀጥታ መዋቅሩና ህብረተሰቡ ጋር የተጀመረው ቅንጅታዊ ሥራ ተጠናክሮ በቀጣይ የጋራ ሠላምና ቤተሰባዊነታችንን ለማየት በትኩረትና ትጋት ልንሠራ ይገባል ስሉም የኮንሶ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ አስታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *