በደቡብ ምዕራብ ክልል የሸካ ዞን ፖሊስ መምሪያ የነብስ ግድያና የወንጀል ትራፊክ አደጋ ምርመራ አስተባባሪ ዋና ሳጅን ወንድማገኝ አለማየሁ እንደገለፁት ተከሳሾቹ የእስራት ቅጣቱ ሊወሰንባቸው የቻለው ህዳር 25 ቀን 2014 ዓ.ም ከረፋዱ 5 ሰዓት በሸካ ዞን የኪ ወረዳ የጻኑ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችውን የ4 አመት ህፃን በመሰውር ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የህፃኗ ቤተሰቦች ለፖሊስ አቤቱታ በማቅረባቸው ፖሊስ በአከባቢው መረጃዎችን ሲያሰባስብ መቆየቱንና ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማድረግ ባደረገው በምርመራ እንዳረጋገጠው አንደኛ ተከሳሽ መለሰ ተመስጌን ህፃኗን ከቤት ጠርቶ ብስኩት እገዛልሻለሁ በማለት ጠርቶ በመውሰድ አቅራቢያ ከሚገኘው ሱቅ ብስኩትና ራኒ መግዛቱንና እስከቀኑ ስድስት ሰዓት አቆይቶ ለሁለተኛ ተከሳሽ ታምራት አለሙ አሳልፎ በመስጠት ሁለተኛ ተከሳሽ የባጃጅ አሽከርካሪ ሲሆን ባጃጅ ውስጥ አስገብተው መውሰዳቸውን በወቅቱ የአይን እማኞች አረጋግጠዋል፡፡

ፖሊስም የምርመራ መዝገቡን በሰው ማስረጃአደራጅቶ ለዞኑ ዐቃቤ ህግ ክስ እንዲመሰረትባቸው መላኩን ተናግረዋል፡፡
ዓቃቤ ህግ በሁለቱ ተከሳሾች ላይ ክስ መስርቶ ፍርድ ቤት ያቀረባቸው ሲሆን የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቴፒ ምድብ ችሎት ግራ ቀኙን ሲያከራክር ቆይቷ፡፡

ፍርድ ቤቱም ሁለቱም ተከሳሾቹ ጥፋተኛ የተባሉት በኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1)ሀ እና በሰው የመነገድና ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1178/2012 አንቀፅ 4(1)(ሀ)ስር የተደነገገውን ህግ በመተላለፍ መሆኑን ጠቅሶ ሁለቱንም ተከሳሾች ጥፋተኛ ብሏቸዋል።

በዚህም መሠረት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቴፒ ምድብ ችሎት ሚያዚያ 4 ቀን 2014 ዓ.ም ባስቻለዉ የወንጀል ችሎት 1ኛ ተከሳሽ መለሰ ተመስጌን በ9 አመት ፅኑ እስራትና በ10 ሺህ ብር 2ኛ ተከሳሽ ታምራት አለሙ በ10 አመት ፅኑ እስራትና 10 ሺህ ብር እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል።
የዞኑ ፖሊስ መርማሪ ወላጆች ልጆቻቸውን ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባቸው አሳስበው ህጻኗ ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ በህይወት አለመገኘቷ የገለፁት መርማሪው አሁን ፖሊስ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ አስረድተዋል ስል የዘገበው ዘገባዉ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ገፅታ ግንባታ ዲቪዥን ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: