በህገ ወጥ መንገድ ከአርባምንጭ ወደ ዎላይታ ሶዶ ስዘዋወር የነበረ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ

በዎላይታ ዞን ጠበላ ከተማ አስተዳደር በህገ ወጥ መንገድ ስዘዋወር የነበረ 10 ኪላሽን ኮቭ ጠመንጃ በቁጥጥር ስር መዋሉን የጠበላ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ።

ኪላሽን ኮቭ ጠመንጃ በህገ ወጥ ዝውውር ከአርባንጭ አድርጎ ወደ ዎለይታ ሶዶ አቅጣጫ ስጓዝ በዎለይታ ዞን የጠበላ ከተማ ፖሊስ ሚያዝያ 03 ከሌሊቱ 9:00 ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ የተያዘ መሆኑን ተገልጿል።

አንዳንድ በአቋራጭ ለመበልፀግ የሚፈልጉ ህገ ወጥ ነጋደወች የገበያ ጉድለትን የምሞሉና ለህዝብ ፍጆታ የሚያገለግሉ ዕቃ ሳይሆን ለዘጎች ፍጅት የሚያገለግሉ በህግ የተከለከሉ ቁሶችን ይነግዳሉ።

ስለዚህ ለሰላማዊ ዓላማና ለልማት በሚውል መኪና ውስጥ ባዕድ አካል በማስበየድ በውስጡ ህገ ወጥ ጦር መሣሪያና ኮንትሮባንድ ያዘዋውራሉና ጎበዝ ነቃ ብሌን የፖሊስ ፍተሻና ብርበራ ሥራን ከመሬት ማድረግ እንደሚገባ ተገልጿል።

ከተለመዱ መኪናወች ውጭ ሁሉንም ዓይነት ተሽከርካሪን በድንገት እንፈትሽ አገርንና ህዝብን ጦር መሣሪያ ከምነግዱ ገዳይ ግለሰቦች እንታደግ ማለታቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *