ወንጀለኛ አካላት ዕርቅ እና ድርድር ፈላጊ በመምሰል ከሕግ የበላይነት ሊያመልጡ አይችሉም – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
ሀገር መከላከያ ሰራዊት ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን በትግራይ ክልል የሚያከናውነው ኦፕሬሽን ዓላማው፣ የሚገባቸውን ቅጣት ሳያገኙ ከገደብ አልፈው የቆዩትን አጥፊ ግለሰቦች እና ቡድኖች በሀገሪቱ ሕግጋት መሠረት ተጠያቂ ማድረግ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡
“ወንጀለኛ አካላት ዕርቅ እና ድርድር ፈላጊ በመምሰል ከሕግ የበላይነት ሊያመልጡ አይችሉም” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት አስተያየት።
