ለወጣቶች ስራ እድል የመፍጠሩን ተግባር እና ለትምህርት ቤቶች የምናደርገውን ድጋፍ አጠናክረን እናስቀጥላለን ሲሉ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ታከለ ታደሰ ተናገሩ።

ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት በወጣቶች ስራ እድል ፈጠራ እና ትምህርት ቤቶችን በመደገፍ ረገድ ዩኒቨርሲቲው ያከናወናቸውን ተግባራት በተመለከተ ለልምድ ልውውጥ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ከመጡ ልዑካን ጋር ከሰሞኑ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።

ከልዑኩ አባላት ጋር በነበራቸው ውይይት ፕ/ር ታከለ እንደገለጹት ከሆነ ተቋማችን የሀገሪቱን የከፍተኛ ት/ት ተቋማት መተዳደሪያ አዋጅ ቁጥር 1152/2011 እንዲሁም የውስጥ አሰራር መመሪያን ከግንዛቤ በማስገባት አካባቢያዊ የልማት ስራዎችን እየሰራን ነው፥ በህጉ መሰረትም በቀጣይ አጠናክረን እናስቀጥላለን ብለዋል።

የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ከመገንባትም ባሻገር አስፈላጊውን ቁሳቁስ እስከማሟላት የሚደርስ ድጋፍ እየተደረገ መቆየቱን የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ፤ በቀጣይ ጊዜያትም ዩኒቨርሲቲው በሚገኝበት ክላስተር ውስጥ በሚገኙ ወረዳዎች 30 በመቶ ድጋፍ ለማድረግ እቅድ መያዙንም አውስተዋል።

በመምህራን ልማት መስክ የመለስተኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚያስተምሩ መምህራን የማስትሬት እና የዶክትሬት ድግሪ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሰፊ ስራ መሰራቱንም ፕ/ር ታከለ ገልጸዋል።

የስራ ዕድል ፈጠራን በተመለከት ፕሬዝዳንቱ ሲናገሩም፣ ለወጣቱ የስራ ዕድል መፍጠር የሁሉም አካል ድርሻ መሆኑን ተናግረው፤ ባሳለፍነው ዓመት ብቻ በተለያዩ ፕሮጀክቶች ከ 5 ሺህ የሚበልጡ ወጣቶችን በጊዜያዊ እና ቋሚ ስራ ላይ ማሰማራት መቻሉን ጠቁመዋል።

በቅርቡም በግቢ ጽዳትና ውበት ማስጠበቅ ስራ ላይበ 13 ማህበራት ለተደራጁና ከአምስት መቶ ለሚበልጡ ወጣቶች የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል ሲሉም ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።

የሕግ ማዕቀፍ በሚፈቅደው አግባብ በቀጣይ ጊዜያትም ከ 4 ሺህ የሚበልጡ ወጣቶችን በተለያዩ የስራ መስኮች በማሳተፍ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑንም ፕ/ር ታከለ ተናግረዋል።

በዩኒቨርሲቲው ኢንተርፕራይዝ ልማት ዘርፍም በርካታ ወጣቶችን አሰልጥኖ ወደ ስራ ለማስገባት እቅድ መያዙን የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ ፤ ህግን ተከትለን በመስራት ተቋማዊ ለውጡን አጠናክረን እናስቀጥላለንም ብለዋል።

የአስተሳሰብ ለውጥ በማምጣት ተቋማችንንም ሆነ ሀገራችንን ለማበልጸግ እንሰራለን ያሉት ፕ/ር ታከለ፤ ሠላምና መረጋጋት የሰፈነበት ምዕዳርን በመፍጠር ዘላቂ ልማትን እውን ለማድረግ ከባለድሻ አካላት ጋር በትብብር እንሰራለን ሲሉም ተናግረዋል።

የልዑኩ አባላትም በዩኒቨርሲቲው እየተተገበረ ያለው ልማታዊ እንቅስቃሴ አድንቀው፤ ያገኙትን ተሞክሮም ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት እንደሚያደርጉ አሳውቀዋል ሲል የዩኒቨርስቲው ኮሙኒኬሽን ዳይሮክተሬት ዘግቧል።

ዘንድሮ ከአራት ሺህ ለሚበልጡ አከባቢ ወጣቶች በተለያየ ሰራ መስክ የስራ ዕድል ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን የዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ አስታወቀ