FB_IMG_1651509776901

በዎላይታ ዞን የሚገነባው አውሮፕላን ማርፊያ ግንባታ ለመጀመር ቤድሮክ ኮንስትራክሽን ድርጅት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕና ከወላይታ ዞን አስተዳደር ጋር የቦታ ርክክብ ውል መፈራረሙን ይታወሳል።

የዘመናት የሕዝብ ጥያቄ የነበረው የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ከአከባቢው ልማትና ኢንቨስትመንት ፍላጎት አንጻር ከፍተኛ መሆኑን ይታወቃል።

ፕሮጀክቱ በዞኑ ውስጥ የሚገኙ በዳሞት ሶሬና በሶዶ ዙሪያ ወረዳ አዋሳኝ ቦታ የሚገነባው ሲሆን ፕሮጀክቱ በተቀመጠለት ጊዜ እንደሚጠናቀቅም ታውቋል።

ፕሮጀክቱ በ150 ሄክታር መሬት ላይ እንደሚገነባና ሲጠናቀቅም ለአካባቢው ማህበረሰብና ለዞኑ ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም ተጠቅሷል።