

“ዱቡሾስ!”
አማዶ ካሬታ ዎላይቶ!
ጋሞ ባይራ ደሬ ናቶ!
ዳውሮ ና’አው ዳንጋርሳው!
አማዶ ካዎ ጋሞ ናታ ጎፋው!
ጋሞ “ባይራ ዴሬ”…ዱቡሻ ሲልህ…እርቅ ማለቱ ነው!…የእውነት መገኛ ቦታዋ ማለቱ ነው!…ደም በይቅርታ የሚደርቅበት የመስዋት ሜዳ ማለቱ ነው!
ለብዙ መቶ ሺህ አመታት የተዘረጋ ስርአት ነው ዱቡሻ በጋሞ!..በሁሉም የጋሞ ደሬ መቶ አመታት ያስቆጠሩ የዱቡሻ አደባባዮች ዛሬም ደምን በይቅርታ እያደረቁ አሉ ህያው ናቸውና!

ዎላይታ “አማዶ ካሬታ ዎላይታው!” ሆላ! ዎላይታ ዱቡሾስ ይላል!..እርቅን ሲጠራ!…ምክክርን ሲጠማው!..ያኮረፍን ከመንጋው ሊቀላቅል!…እውነትን ፈልጎ ሊያገኝ!…ቀዬው እንዴት ውሎ አድሯል ሊል!…ለሀገር ሰላም ሊሰብክ ሰላምን ሊጠራ…አኔ ዱቡሾስ ይላል አማዶ ወላይታ!… ጋሌ ከኮይሻ…ዳሞቴው ከሁምቦው!..ገሱባ ከሶሬው!..ሁሉም ለማንነቱ ዱቡሻ ተቀምጦ ሀገር አቁሟል ነገም ያስቀጥላል!..

ዳውሮ “ዳውሮናይ ዳንጋርሳው!”..እሱም እንደ ወንዱሞቹ ዱቡሾስ ይላል!..ፍቅርን ሲጠራ..ክፍን ሊያባርር…የዘመመ ቤት ሊያቀና!..የተበተነ ጎጆ ሊሰበስብ!..የተቸገረን ሊረዳ!.. የተጣሰ ድንበርን ሊያስከብር!..ለነዚህና መሰል የህልውና ችግሮች የሀላላ ልጆች ለረጅም ዘመናት ዱቡሻ ተቀምጠው ሰላም አውርደው ሰላምን ሰብከው ኖረዋል…ለዘለአለምም ይኖራሉ!…

ጎፉ “አማዶ ካዎ ጋሞናው ጎፎ!…ዱቡሾስ ይላል እሱም እንደ እናት ልጆቹ እንደ ወንዱሞቹ!…ዱቡሻ በጎፋ ይለያል!.. የካዎ ጋሞ ልጆች ያለ ዱቡሻ እዚህ አልደረሱም!.. የተበደለ የሚካስበት!..የፈረደበት ከሸክሙ የሚቀነስለት!..ሀቅ ቀና ብላ ሀሰት አንገቷን የምትደፋበት!..የብዙዎች እባ የሚታበስበት!..ተንበርክከህ ለይቅርታ የምታለቅስበት መድረክ ነው ዱቡሻ!…በነዛ በደጋጎቹ ጎፋዎች ሰፈር!

ዱቡሻ ለእነዚህ ህዝቦች ካሏቸው በርካታየጋራ እሴቶች አንዱ ነው!..የጋራም ሆኖ ይቀጥላል!
በጅረኛ ቲ ጀፈረሳ
አኔ ኢሲፔ “ኑኒ ኢሲኖ ጊቴ!..” ታ አያ ናቶ!
አማዶ ካሬታ ዎላይቶ!
ጋሞ ባይራ ደሬ ናቶ!
ዳውሮ ና’አው ዳንጋርሳው!
አማዶ ካዎ ጋሞ ናታ ጎፋው!
