በደቡብ መንገዶች ባለስልጣን የዎላይታ ሶዶ ዲስትሪክት የመንገድ ግንባታና ጥገና ስራዎች በታቀደላቸው ጊዜ እየሄዱ መሆኑ ተገልጿል።

የደቡብ መንገዶች ባለስልጣን የሶዶ ዲስትሪክት የስራ እንቅስቃሴ የደረሰበትን ደረጃ በተጎበኘበት ወቅት የሶዶ ዲስትሪክት ስራ አስኪያጅ አቶ ጳውሎስ ጩምኣ እንደገለጹት የሶዶ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ሁለት ዞኖችን እንዲሁም ወላይታ፣ጋሞና ጎፋ የሚያገናኝ አንድ መንገድ እና በአጠቃላይ በዲስትሪክት ጽ/ቤቱ በ2014 በጀት አመት 14 ፕሮጀክቶች ታቅደው እየተሰሩ እንዳለና የአፈፃፀም ደረጃቸው በተለያየ ሁኔታ ያለ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህ በጀት አመት 158 ኪሎ ሜትር መንገድ ለመስራት ታቅዶ እየተሰራ እንደሆነና ከእነዚህም 4 የመንገዶች ፕሮጀክቶችን መሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ እየሰራን ነው ብለዋል።

ሶዶ፣ ቡልቡላ፣ ሆብቻና አባያ ፕሮጀክት 40 ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የተለያዩ ዞኖችን ዎላይታ፣ ሲዳማና ጌዲኦ ዞኖችና የሚያገናኝ መንገድ እነዚህን ዞኖች ማህበረሰብ በተለያዩ ጉዳዮች ግንኑነት እንዲጠናከር እና ኢንቨስትመንት ያለበት አካባቢ እንደመሆኑ መጠን በህብረተሰቡ ዘንድ ማህበራዊ ትስስር እንዲጠናከር የሚያስችል መንገድ እንደሆነ አብራርተዋል

በበጀት አመቱ 300 ኪሎ ሜ ትር በቁጥር 15 መስመር ለጥገና እና 6 በራስ አገዝ የሚገነባ ድልድይ ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸው 10 በውጭ ኮንትራክተሮች የሚሰሩ ድልድዮች እንዳሉም ጠቅሰዋል ።

መንገዱ ሳይገነባ በፊት ምርት አምርተን ለገበያ ለማቅረብ፣ወላድ እናቶች ወደ ጤና ተቋም ለማድረስም ሆነ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ ለመማር የማይቻልበት ግዜ ነበር አሁን ግን ከለውጥ ወዲህ ይህ ችግር ሁሉ ስለተቀረፈልን በጣም ደስተኞች ነን ሲሉ ከአካባቢው ማህበረሰብ አንዳንድ ያነጋገርናቸው አካላት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ሰል የክልሉ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: