
ወንጀለኛ ወጣት ገላዬ ግንበሩ ገዜ አድራሻው በጋሞ ዞን ምዕራብ ዓባያ ወረዳ ደጋ ዶኔ ቀበሌ ግግማ በሚባል ልዩ መንደር ይኖር የነበረ ጥር 11/2011/ዓ ም አንዲት የአምስት ዓመት ህፃን ሶሲና መስፍን የተሰኘች መስማት ከተሳናቸው አያታቸው ጋር የምትኖር ሲትሆን ሌሊት ቤት ሰብሮ በመግባት ተኝታ ባለችበት የመድፈር ወንጀል ፈጽሟል።
ወንጀለኛውን በአከባቢው ህብረተሰብ ርብርብና በወረዳው ፖሊሶች ብርቱ ክትትል በሕግ ቁጥጥር ስር ልውል ተችሏል።
የህፃኗ ሕይወት በወረዳው ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት እስከ ክልል ድረስ ትስስር በመፍጠር ሕይወቷ ልተርፍ ችሏል። በአሁኑ ሰዓትም ህፃኗ ሙሉ በመሉ ጤናማ ሆና በሀዋሳ ህፃናት ማሳድጊያ በመንግስት ድጋፍ በማግኘት ትምህርቷን በመከታተል ላይ ትገኛልች።
ወንጀለኛውም በቀን 23/09/2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰው ማስረጀና በሐክም ማስረጃ የተደራጀና የተደገፈ ቢሆንም ወንጀለኛው ድርጊቱን በመፈፀሙ የወረዳው ፍ/ቤት በዋለው ችሎት ባመነው መሠረት የ21 ዓመት ጽኑ እስራት ውሳኔ አስተላልፏል።
ውሳኔውም የዘገዬበት ምክንያት የህፃኗ ጤንነት እስክረጋገጥ ድረስና የሕክምና ውጤት እስከምስጥ መዘገየቱን ዋና ኢንስፔክተር ጌታቸው እንዳለ ገልፀዋል ስል የምዕራብ አባያ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዘግቧል።