እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ🤲

ሃገሬ ኢትዮጵያ ግብፅን በፍፁም የበላይነት በማሳየት በአፍሪካ ዋናጫ ማጣሪያ በከፍተኛ የኳስ ብልጫ ጋር የሁልጊዜ ተቀናቃኝ የሆነችውን ግብፅን 2 ለ 0 አንገት በማስደፋት አሸንፋለች።

ይሄ አሽናፊነት ለኢትዮጵያ የእግር ኳስ ብቻ ሳይሆን ዘርፈብዙ አሸናፊነት በመሆኑ ብዙዎች ደስታቸውን መቆጣጠር አልቻሉም።

በጨዋታው መጀመሪያ አጋማሽ ዳዋ ሁጤሳ እና ሽመልስ በቀለ ካስቆጠሯቸው ጎሎች በተጨማሪ አቡበከር ናስር ድንቅ ሙከራ አድርጓል። አቡበከር ያስቆጠራት ጎልም ከጫዋታ ውጪ ተብላ ተሽራለች።

በዚህም በኢትዮጵያ ግብፅ የተወሰደባትን ብልጫ ለመቀልበስ ገና በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለት ተጫዋቾችን ለመቀየር ተገዳለች።

በመጀመሪያ አጋማሽ ጨዋታው ኢትዮጵያ 9 ሙከራዎችን ስታደርግ ግብፅ በመጀመሪያው አጋማሽ ምንም አይነት የጎል ሙከራ አላደረገችም።

ምንም እንኳ ኢትዮጵያ ይህን ጨዋታ ከሜዳዋ ውጪ በባዕድ አገር ሜዳ እንድታደርግ ብትገደድም ዋሊያዎቹ ከአገሪቱ ዜጎች እና ትንሽ ከማይባሉ በስታዲየም ከተገኙ ኢትዮጵያውያን ተመልካቾች ድጋፍ ተችሯቸዋል።

ኢትዮጵያ ለ2023ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከማላዊ፣ ከጊኒ እና ከግብፅ ጋር መመደቧ ይታወቃል።

ኢትዮጵያ ዛሬ በልጆቿ ኮርታለች❤

የዎላይታ ታይምስ ኢትዮጵያን እንኳን ደስ አለን፣ እንኳን ደስ አላችሁ ይላል🤲

ኢትዮጵያ 🇪🇹 2 ግብፅ 🇪🇬 0

Full Time

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: