በቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት በሲዳማ ክልል ሀኮ ወረዳ የተገነባው 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተጠናቆ ተመርቋል፡፡

ትምህርት ቤቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በተገኙበት ነው የተመረቀው።

ትምህርት ቤቱ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የመጽሐፍ ሽያጭ በተገኘው ገቢ በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት የተገነባ ሲሆን፥ ለግንባታውም 11 ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጎበታል።

ትምህርት ቤቱ 12 የመማሪያ ክፍሎችን ጨምሮ ሁለት ቤተ ሙከራ እና አንድ ቤተመጻሕፍት አለው።

በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፣ የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዳይሬክተር ኢንጂነር ሃብታሙን ጨምሮ የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት በሲዳማ ክልል የመጀመሪያውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው ያስመረቀው።

ፅህፈት ቤቱ በሁለተኛው ዙር ካስገነባቸው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ይህ ሶስተኛው ሲሆን በጥቅሉ 23 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን አስመርቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: