1656174246310

በዞኑ በወናጎ ከተማ ከ85 ሺህ ሊትር በላይ ቤንዚን ከባዕድ ጋር ቀላቅሎ ለህብረተሰቡ ስሸጥ የነበረ ኦይል ሊቢያ ማደያ ማሸጉን የጌዴኦ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታውቋል።

የዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያው እንዳስታወቀው  ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት በወናጎ ከተማ ከ85 ሺህ ሊትር በላይ  ባዕድ ቀላቅሎ ለህዝቡ ስሸጥ የነበረ ማደያ እንደነበር ደርሼበታለሁ”ም ብለዋል።

የጌዴኦ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ሃላፊ ወይዘሮ ምስጋና በራሶ እንዳስታወቁት መንግስት የህዝብን ፍላጎት ለሟሟላት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የነዳጅ አቅርቦት ለማህበረሰቡ ተደራሽ እንዲሆን  በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።

ህገወጥ ንግድ ለመከላከል በትኩረት እየሰራ የሚገኘው የዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ከወናጎ ከተማ አስተዳደር ጋር በጋራ በመሆን ከህዝቡ ባገኘነው ጥቆማ መሠረት ለህብረተሰቡ ከባዕድ ተቀላቅሎ ስሸጥ የነበረ ነዳጅ የማጣራት ስራ ለማጠናከር ባደረገው ጥልቅ ክትትል ቤንዚኑ የጥራት ጉድለት እንደነበረ ከኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ለማጣራት ችሏል።

የወናጎ ምክትል ከንቲባና የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ስንታየሁ ጎሎ በከተማ እየተበራከተ የመጣውን ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴና ከደረጃዎች በታች የሚመጡ ምርቶችን የመቆጣጠር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

በዚህም መሠረት ከ85 ሺህ ሊትር በላይ ቤንዚን ከባዕድ ጋር ቀላቅሎ ለህብረተሰቡ ስሸጥ የነበረ በኦይል ሊቢያ ማደያ ላይ ጥልቅ ክትትል በማድረግ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስደዋል ብለዋል።

ህገወጥ ተግባራትንና መሰል ችግሮች ለመቅረፍ ከተማ አስተዳደሩ ከዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ጋር በጋራ በመሆን የክትትል ስራ አጠናክረው እንደሚቀጥል አቶ ስንታየሁ ገልጸዋል።

የንግዱን ስርዓት ለማዛባት በርካታ ህገወጥ ነጋዴዎች በዞኑ እየተበራከተ መምጣታቸውን የገለፀው የጌዴኦ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ህገወጥ ተግባር ለመቆጣጣር በሚደረገዉ ጥረት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ  ጥሪ በማቅረብ ከ85 ሺህ ሊትር በላይ ቤንዚን ከባዕድ ጋር ቀላቅሎ ለህብረተሰቡ ስሸጥ  የነበረ ኦይል ሊቢያ ማደያ ማሸጉን አስታውቀዋል ስል የዞኑ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ያደረሰን ዘገባ ያመለክታል።