1656420847747

በከተማው በዋና ዋና መንገድ ዳር የሚገኙ ሆቴሎችና ንግድ ቤቶች ከይዞታቸው አልፈው በህገወጥ አካሄድ የሰሩትን ቤትና ዳስ የማፍረስ እርምጃ በሁሉም አቅጣጫ ተጠናክሮ መቀጠሉን በዛሬው ዕለት የWT ሚዲያ ባደረገው ቅኝት ለማረጋገጥ ችሏል።

የተለያዩ ግለሰቦች ከህጋዊ ይዞታቸው አልፈው በህገወጥ አካሄድ የሰሩትን ቤትና ዳስ የማፍረስ እርምጃ አወሳሰድ ተገቢና ወቅቱን የጠበቀ መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች አስረድተዋል።

በተለይም ግለሰቦቹ ከህጋዊ ይዞታቸው አልፈው የሚሰሩት ስራ ህገወጥነትን ከማባባስ በተጨማሪ ያልተገባ ጥቅም ባማስገኘት መንገድን በመዝጋት የትራፊክ አደጋዎችን እያደረሰ እንዲሁም ለከተማ ውቤት አሉታዊ አስተዋፆኦ እያበረከተ መሆኑንም ገልጸዋል።

እየተወሰደ የሚገኘው የህግ ማስከበር እርምጃ በከተማዋ በሁሉም አከባቢዎች ያለምንም ልዩነት እየተካሄደ መሆኑ እንዳስደሰታቸውም ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች አክለው ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገውና
ከይዞታቸው አልፈው በህገወጥ አካሄድ የሰራው ቤት በህጋዊ መንገድ እንዲፈርስ የተደረገው ግለሰብ እርምጃ ተገቢ መሆኑን በመግለፅ ከሚመለከታቸው አካላት በቂ ቅድመ ማስጠንቀቂያ መስጠት መሰጠት ነበረበት ብለዋል።

በከተማዋ በሁሉም አከባቢዎች ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ከይዞታቸው አልፈው በህገወጥ አካሄድ የሰሩትን ቤት በባለሙያዎች ቅደመ ጥናት ተለይቶ ህጋዊ እርምጃ የመውሰድ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን የሶዶ ከተማ ማዘጋጃዊ ቤት ፅ/ቤት ኃላፊ እ/ር ብዙአየሁ ወልዴ ተናግረዋል።

ከተማውን ፅዱና ማራኪ ለማድረግ እየተወሰደ የሚገኘውን ህጋዊ እርምጃ ሁሉም ህብረተሰብ ክፍሎች የበኩሉን ሚና መጫወት እንዳለበትና ያንን ለማስፈጸም ኮሚቴ ተወቅሮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ፍትሀዊነትና ግልፀኝነት በተሞላ አካሄድ በቅንጅት እየሰራ ስለመሆኑም እ/ር ብዙአየሁ አክለው ገልጸዋል።