ለቀድሞ ሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ ለነበሩት አቶ ቃሬ ጨዊቻ ከሲዳማ ዘንድ የፍቅር ስጦታ ተበረከተ

በቀን 23/10/14 በሀዋሳ ሳዉዝ ስታር ሆቴል የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የአቶ ቃሬ ጫዊቻ ወዳጆች እንድሁም ኤጄቶዎች(የሲዳማ ወጣቶች) በተገኙበት ዘመናዊ የመኪና ስጦታ ተደርጎላቸዋል።

አቶ ቃሬ ጫዊቻ በሰፊው ሲዳማ ህዝብ ዘንድ የሚወደድ እና የሚከበር ሰዉ መሆናቸው ይነገርላቸዋል።

የሲዳማ ህዝብ በክልል ለመደራጀት በሚያደረገው ትግል ወቅት ላይ <ታግለን እንጅ ለምነን የሚንወስደዉ ክልል የለም።> በማለታቸው ከህዝቡ ጎን መሆናቸው በተግባር ያሳዩ ጀግና ሰዉ መሆናቸው በህዝቡ ዘንድ ይነገርላቸዋል።

አቶ ቃሬ ጨዊቻ በጤና ዘርፍ ከወረዳ አንስተው እስከ ፈዴራል የጤና ሚንስትር ዴታ ድረስ በሀላፊነት የሰሩ ስሆን በሰሩት ስራ ደግሞ በቅርቡ መሸለማቸው የሚታወስ ነው።

በአሁን ሰዓት አቶ ቃሬ የ PhD ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ እንደሚገኙ ከቤተሰቦቻቸው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *