

የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ 2014 ዓ.ም የፊዚክስ እና የሂሳብ ትምህርት ተመራቂው ራጂ አሸናፊ 60 የትምህርት አይነቶችን A+ በማምጣት ታሪክ ሰርቷል።
አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስኮች ሲያሰለጥናቸው የቆዩ 1 ሺህ 253 ተማሪዎችን አስመርቋል።
የ25 አመቱ ወጣት ራጂ በአዳማ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የፊዚክስ እና የሂሳብ ትምህርት ተመራቂ ሲሆን በ60 የትምህርት አይነቶች A+ በማምጣት አስገራሚ ውጤት አስመዝግቧል።
ራጂ ተወልዶ ያደገው ቄለም ወለጋ ጊዳሚ ከተማ ሲሆን የ10ኛ ክፍል ውጤቱ በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች A እንደነበር እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤቱም 647 እንደነበር ተገልጿል።
በዓለም ላይ ካሉት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ግንባር ቀደም የሆነው ኤም አይ ቲ ራጂ እስከ ፒ ኤች ዲ ድረስ በዩኒቨርሲቲው ተቀላቅሎ እንዲማር ነጻ የትምህርት እድል ለመስጠት ቃል እንደገባላቸውም የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ለሚ ጉታ ተናግረዋል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል።
