ላለፉት ሶስት ዓመታት ተኩል ያህል የኢትዮጵያ ቱሪዝምና ሆቴል ማሰልጠኛ ተቋም በዋና በዳይረክተርነት ሲያገለግሉ የቆዩት ወ/ሮ አስቴር ዳዊት በዛሬው ዕለት ለአዲሶቹ አመራሮች፣ ለነባሮቹም እንዲሁም ለማኔጅመንት አባላቱ የመውጪያ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በጅምር ያሉ ስራዎችን እና የተቋሙን የ53 ዓመት ዋናዋና ጉዞዎች አስተዋውቀዋል፡፡

የተቋሙ አመራሮችና የማኔጅመንት አባላቱም ለወ/ሮ አስቴር ያላቸውን አክብሮትና መልካም የስራ ጊዜ ተመኝተዋል፡፡

ወ/ሮ አስቴር ዳዊት በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ም/ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተመድበዋል፡፡

አዲስ የተሾሙ አመራሮችና የቀድሞ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ከማኔጅመንት አባላቱ ጋር ይፋዊ ተውውቅና የስራ ርክክብ ማድረጋቸውን ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወይዘሮ አስቴር ዳዊት ከዞን አመራርነት ጀምረው በክልል፣ በፌደራል ሚኒስቴር ዴኤታነት ኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉና ልምድ ያካበቱ ናቸው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *