ወጣት ብሩክ በቀለ ይባላል፣ የዎላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪ ሲሆን በዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ መካኒካል እንጂኔሪንግ ተማሪ ነው ። በምስሉ የሚታየውን EW-13(Ethiopia#Wolaita-13) የሆነችውን አነስተኛ ሄለኮፕተር እየሰራ የሚገኘውን ይፋ አድርጓል።
ባለፈው በአረካ በከተማዋ አንድ ወጣት በተመሳሳይ ሁኔታ የሰራትን መለስተኛ ሄለኮፕተር በከተማዋ ወጣቶች መዝናኛ ማዕከል ላይ የሙከራ በረራ ለማድረግ ቢታቀድም እንዲሁም የሙከራ በረራ ለመመልከት የመጡ በርካታ ስዎች የተገኙ ቢሆንም የዘርፉ ባለሙያዎች ስለሌሉ አደጋ ልያደርስ ይችላል በሚል በከተማ አስተዳደሩ ለጊዜው እንዲሰረዝ መደረጉን እናስታውሳለን።
ከዚህ በፊት በዎላይታ ሶዶና አረካ ከተማ ወጣቶች ስካቫቴርና አድስ ሞዴል መኪና መስራታቸውን እናስታውሳለን።
በመሆኑም ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በተላይም ዩንቨርስቲ፣ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት የፈጠራ እውቀት ያላቸውን የተለያዩ ወጣቶችን በማደራጀት የፈጠራ እውቀትን ተጠቅሞ ራሳቸውን፣ አከባቢውን ሆነ ሀገሪቷን መጥቀም የሚችሉበት ሁኔታ ቢያመቻቹ መልካም ነው እንላለን።
