
“የደቡብ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት ስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከሐምሌ 14 ጀምሮ ያካሄዳል” አፈ ጉባኤ ፋጤ ሶርሞሎ
የደቡብ ብ/ብ/ህ/ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር አንደኛ ዓመት ስራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን ከሐምሌ 14 ጀምሮ እንደሚያካህድ የምክር ቤቱ ዋና አፈ ፋጤ ሶርሞሎ ገለጹ
//eephaush.com/4/5235241
የምክር ቤቱ ከነገ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 16 በሚያካህደው ጉባኤ የ2014 በጀት ዓመት የአስፈጻሚ አካላት እቅድ አፈጻጸምና 2015 እቅድ ቀርቦ እንደምወያይ ገልጸዋል።
የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የዋና ኦድተር መስሪያ ቤት የተጠናቀቀውን በጀት ዓመት አፈጻጸምና እቅድ እንደምያቀርቡና ውይይት እንደምደርግ አፈ ጉባኤ ፋጤ ጠቁመዋል።
ምክር ቤቱ በመደበኛ ጉባኤው የ2015 በጀት የእቅዶች ማስፈጸሚያ በጀት ጨምሮ ሌሎች አጀንዳዎችን ማዘጋጀቱንና የጸደቁ አጀንዳዎች በነገው ዕለት ለምክር ቤቱ አባላት እንደምደርሱም ክብርት አፈ ጉባኤ ጨምረው ገልጸዋል።