Photo_1658509030355

በደቡብ ክልል በአማሮ ልዩ ወረዳ ከ77 ሺህ በላይ ህዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልግ የልዩ ወረዳ ግብርና ፅ/ቤት አስታወቀ።

የልዩ ወረዳ ግብርና ፅ/ቤት አደጋ ስጋት አመራር ቅድሜ-ማስጠንቀቂያ ዘርፍ ባለሙያ የሆኑት አቶ አዳሙ አረዶ እንደገለፀት፤-በምዕራብ ጉጂ ዞንና በአማሮ ልዩ ወረዳ መካከል በተፈጠው ግጭት አከባቢያቸውን ለቀው የተፈናቀሉት በአጠቃላይ 44ሺህ 2 መቶ በላይ እንደሆሁና እስከ አሁን ከ10 ሺህ 9መቶ በላይ የሚሆን ሰው በሻራ ውስጥ ከመኖራቸውም በተጨማሪ ከ33 ሺህ 240 በላይ ሰዎች አቅም ያላው ተከራይቶ አቅም የሌለው ወደ ሰው ተጠግቶ አሊያም ቀን ሥራ እየሰሩ መኖራቸውን ገልፀው።


በዘንድሮ በልግ ምርት ትመና መሠረት 25 በመቶ ምርት ሊገኝ እንደሚችል መገመቱንና ከዚህ የተነሳ በድርቅ ሳቢያ ተጨማሪ 33ሺ 240 ሰዎች ለረሀብ መዳረጋቸውን ተናግረዋል።

በአማሮ ልዩ ወረዳ አጠቃላይ በግጭትና በድርቅ ምክንያት ከ77ሺህ 440 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በረሀብ አደጋ ውስጥ መግባታቸውንገልፀው፤ አስቸኳይ እርዳታ ካልተደረገ በሰው ህይወት ከፍተኛ እልቅት ሊያስከት በሚችል ሁኔታ ውስጥ በመሆኑ ታውቆ መንግስት፥ መንግስታዊ ያልሆኑ ረጂ ድርጅቶ፥ ባለሀብቶችና በሌላ አከባቢ የሚትኖሩ የወረዳ ተወላጆች የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የጃሎ ሊ/መንበር የሆኑት አቶ ሰብሰቤ ቸርነትና ሌሎች የቀበሌ አርሶ አደሮች የሆኑት ወ/ሮ ታደለች ተስፋየ እና ርብቃ አርጓዴ በጋራ በሰጡት አስተያየት እንደገለፀት፤- በምዕራብ ጉጂ ዞንና በአማሮ ልዩ ወረዳ መካከል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት አከባቢያቸውን ለቀው ከተፈናቀሉና ሻራ ውስጥ መኖር ከጀመሩ 6 ኣመታት ማስቆጠራቸውንና ከግጭቱም በተጨማሪ ባለፉት 3 ተከታታይ ምርት ወቅት ድርቅ ፥ የአንበጣ መንጋ እና የተምች ክስተት በመኖሩ አብዘኛ የቀበሌነዋሪዎ ቀያቸውን ለቀው እስከ መሰደድ ደርሰዋል ብለዋል።

ድርቁ በዚሁ ከቀጠለ ህዝቡ ላይ በግጭቱ ሳቢያ ከቀብሌያቸው ከሞተው ህዝብ በላይ በአንድ ጀምበር በርካታ ሰው ሊሞት እንደሚችል የተናገሩ ነዋሪዎቹ ፥አሁን አሁን በየጤና ተቋማት ያለው የጃሎ ቀበሌ የህፃናትና፥አረጋዊያን እና ሴቶች ቁጥር በየጊዜ እየጨመረ መጥተዋል ብለዋል።


መንግስት እያደረገ ያለው ድጋፍ በቂ ካለ መሆኑም በተጨማሪ በግጭቱ ሳቢያ መንገድ ከመዘጋት ጋር ተያይዞ በየጊዜ መቆራረጦች እንዳለ የገለፀት ነዋሪዎቹ፤- በአከባቢ ያለውን የፀጥታ ሁኔታ መንግስት በማስፈን ወደ ቀያቸው በዘላቂነት እንዲመልስና በምግብ ራሳቸውን እንዲችሉ ድጋፍ እንዲደረግ ሲሉ ጠይቀዋል።

የአማሮ ልዩ ወረዳ ግብርና የፅ/ቤቱ ም/ሀላፊና የእርሻ ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት አቶ ከፍያለው አዱላ እንደገለፁት በ2013/14 የልግ እርሻ ወቅት ከ24ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በበልግ ለመሸፈን ታቅዶ 18ሺ በላይ መሸፈኑን ገልፀው፥ የዘንድሮ ዝናብ ዘግይቶ የመጣና ስርጭቱም የተስተካከለ ካለመሆኑ የተነሳ ተምችና ድርቅ በመከስቱ የታሰበውን ያክል ምርት ማግኘት እንዳልተቻለ ገልፀው፥ በድርቅ ምክንያት በቆሎና ጤፍ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መጥፋቱን ተናግረዋል።


አቶ ጎሹ ጌታቸው የአማሮ ልዩ ወረዳ ግብርና የፅ/ቤቱ ሀላፊ በበኩላቸው የአማሮ ህዝብ ለ3 ተከታታይ የምርት ዘመን በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች የተፈራረቀበት ህዝብ እንደሆነ ገልፀው፤ በ2013/14 ምርት ዘመን የዝናብ ሁኔታ ወጣገባ ያለ፥ ነፋስ የተቀላቀለ እና እየተቆራረጠ የሚመጣ ከመሆኑም በተጨማሪ ተምችየተከሰተ በመሆኑ ምርቱ ሙሉ በሙሉ በመጥፋቱ
በወረዳችን በተለይ በቆላማ ቀበሌያት ያሉ ከፍተኛ ቁጥር የያዙ ህፃናት፥ አረጋዊያንና ነብስ ጡር ሴቶች በምግብ እጥረት ችግር ላይ ናቸዉ ብለዋል።

ዘገባው የአማሮ ልዩ ወረዳ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነዉ።