
የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ዎሕዴግ) ኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚቴ ጠቅላላ ጉባዔ ለማድረግ ለምርጫ ቦርድ ላቀረበው ጥያቄ ከቦርዱ ውሣኔ ተላለፈ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቁጥር 1162/11/678 በቀን ሐምሌ 13/2014 ዓ.ም ለዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ዎሕዴግ) ኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚቴ በጻፈው ደብዳቤ በሕጉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ጠቅላላ ጉባኤ ካላደረጉ ፓርቲዎች ዎሕዴግ አንዱ ነው ብሏል።
በፓርቲው አመራሮች መካከለል በፈጠረው አለግባባት ምክንያች የፓርቲው ሊቀንበር በቦርዱ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ እስከ ሰኔ 10/2014 ዓ.ም መሠረት ጠቅላላ ጉባኤውን መጥራት እንዳልቻሉ ከቦርዱ የተጻፈው ደብዳቤ ያመላክታል።

የኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚቴ የተፈጠረው አለግባባት የግንባሩን ሕልውና የሚያናጋ እና አስጊ ወደ ሆነ አቅጣጫ የሚያመራ በመሆኑ ችግሩን በጉባኤ ለመፍታት ጠቅላላ ጉባኤ ለመጥራት የወሰነ መሆኑን ገልጾ ቦርዱ ታዛቢ እንዲልክለት መጠየቁ ተጠቅሷል።
ቦርዱ ሐምሌ 13 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ከሁለቱም ወገኖች ሲቀርቡ የነበሩትን አቤቱታዎች በአዋጁ እና በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት መመርመሩን ጠቁሟል።
በዚሁ መሠረት ሊቀመንበሩ በመዳደሪያ ደንቡ እንቀፅ 17 መሰረት በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤውን ለመጥራት ያልቻሉ መሆኑን አረጋግጧል።
በመሆኑም ፓርቲው ኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚቴ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ፣ የኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚቴ ጠቅላላ ጉባኤው የሚካሄድበትን ቀንና ቦታ ወስኖ ለቦርዱ እንዲያሳውቅ፤ ኮሚቴው ሰኔ 13/2014 ዓ.ም. ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ጋር ተሰብስቦ ያቋቋሙት የጠቅላላ ጉባኤ አደራጅ ከሚቴ የዝግጅት ስራውን እንዲቀጥል፤ ማሻሻያ የሚደረግበትን የመተዳደሪያ ደንብ ረቂቅ እስቀድሞ ለቦርዱ እንድልክ ቦርዱ ጠይቋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ሊቀመንበር አቶ ተክሌ ቦራና ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ “ከምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ደርሶናል፣ ጠቅላላ ጉባኤ ለማድረግ ከእኔ ጋር ካሉ ሰዎች ጋር አልተናጋገርነበትም” የምል አጭር ምላሽ ሰጥዋል።

በሌላ በኩል የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ዎሕዴግ ህጋዊ ሊቀመንበር የሚሉ አቶ ጎበዘ ጎኣ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በጉዳዩ ዙሪያ በሰጡት ሀሳብ “ምርጫ ቦርድ ማስተካከያ አድርገን ጠቅላላ ጉባኤ እንድናደርግ ደብዳቤውን በአድራሻችን ልኳል፣ ግንባሩ ዎላይታ ሶዶ ውጪ ሌላ ሊቀመንበር የለውም፣ አቶ ተክሌ ቦራና አመራር ሳይሆን አባል ነው፣ በጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደማንኛውም አባል ልሳተፍ ይችላል” ብለዋል።

“በምርጫ ቦርድ በተጠየቅነው መሠረት ጠቅላላ ጉባኤውን በቅርቡ ለማካሄድ እየተነጋገርንበት ነው” በማለት አቶ ጎበዜ ገልጸዋል።
ከምርጫ ቦርድ በኩል የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ህጋዊ ሊቀመንበርነት ውዝግብ በተመለከተ ማግኘት አልቻልንም።