በዎላይታ አከባቢ በክብር ተሰናባች የመከላከያ ሠራዊት አባላት በህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ/ህወሐት/ ዉስጥ በሚገኙ አርመኔ ቡድን በኢፌድሪ የመለካከያ ሠራዊት ላይ የተፈፀመዉን ኢ-ሰባአዊ ድርግት እንቃወማለን በማለት፣ ይህ ሠራዊት ከቡሬ አይሞከር ተራራ አንስቶ እስከ ሽራሮ 1000 ኪ.ሜ እንደ አጥር ራሱን አጥሮ ለኢትዮጵያዊያን በተለይም ለትግራይ ህዝብ አለኝታ በመሆን ራሱን መስዋት ስያደርግ በነበረዉ ኃይል ላይ በታርክ ይቅር የማይባል ድርግት መፈጸሙን እኛ ከመከላከያ በክብር የተመለስን የሠራዊት አባላት እጅግ በጣም ያስደነገጠንና ያስቆጣን ስለሆነ ፣ በዚህ ዙሪያ በመንግስት ጎን ለመሰለፍ ባለ ስምንት(8) ነጥብ የአቋም መግለጫ አዉጥተዋል፡፡
በዚህ ባረጀና በጡረተኛ ብድን ላይ የሚወሰድ ማነኛዉም እርምጃ እንደግፋለን፣
ይህ ቡድን እስካለ ድረስ በኢትዮጵያ ሰላም ስለማይኖር በመንግሥት በኩል ድርድር የሚባል ሀረግ እንዳይታሰብ አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡
ይህ ቡድን በጥፋቱ መጠን ቅጣቱን እንዲያገኝ እንጠይቃለን፡፡
እኛ የቀድሞ መከላከያ በክብር ተመላሽ ሠራዊት መንግሥት በሚያደርገዉ ጥር ለመመለስ በተጠንቀቅ ቆመናል፡፡
በአገራችን ህግ-መንግሥት የትግራይ ክልል አምባገነን አመራሮች ህገ-መንግሥት የመናድ ተግባርን እኛ የክብር ተሰናባች መከላከያ ሠራዊት ይቃወማል፡፡ እንዲሁም በመንግሥት ጎን በመቆም ህገ-መንግሥቱን ከአደጋ ለመከላከል ዝግጁ መሆናችንን እንገልጻለን፡፡
ይህን ምክንያት በማድረግ በከተማችን በፀጥታ ሁኔታ የሚፈጠረዉን ችግር ከመንግሥት አካል ጎን በመሆን የህዝባችንን ፀጥታ ለመጠበቅ ዝግጁ መሆናችንን እንገልጻለን፡፡
በህዝብ አመራሮች ላይ የምነሳዉን ጫና በጋራ ለመከላከል ዝግጁ መሆናችንን እንገልጻለን፡፡
በመንግሥት ተቋማት እና በግለሰቦች ተቋማት ላይ የሚፈጠሩትን አደጋዎች በህዝብ ጎን በማቆም ፀጥታ ለማስጠበቅ ዝግጁ መሆናችንን እንገልጻለን ብለዋል፡፡
🇪🇹ክብር ለመከላከያ ሠራዊቶቻችን!!!!!
