IMG_20220929_150153_153~2

በዎላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ አንድ አባት የራሱን፣ የልጁንና የልጅ ልጁን ህይወት ማጥፋቱን የቦዲቲ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የጽህፈት ቤቱ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ወልዴ ቢሊሶ፤ አቶ አምዴ ሙሳ የተባለ ግለሰብ የራሱን ህይወት ጨምሮ የሶስት ሰው ህይወት ማጥፋቱን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልጸዋል።

ግለሰቡ ከዚህ ቀደም አልፎ አልፎ ከባለቤታቸው ጋር አለመግባባትና ግጭት ይፈጠር እንደነበር መረጃዎች እንደምጠቁሙ ገልጸዋል።

17/01/2015 ዓ.ም ረፋድ ላይ ወልዳ እቤት ውስጥ የተኛች የ28 ዓመት አራስ ልጁንና የ5 ወር ልጇን ጨምሮ መግደሉን ነው የገለጹት።

በመቀጠል ግቢ ውስጥ ባለው ውሃ በትልቅ የውሃ ገንዳ ውስጥ በመግባቱ የግለሰቡ ህይወት ማለፍ መቻሉን ተናግረዋል።

የወንጄሉን ምክንያት ፖሊስ በማጣራት ላይ እንደምገኝም ምክትል ኢንስፔክተር ወልደ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በስልክ አስረድተዋል።