received_397353602596656

ስለ ዎላይታ ዲቻ ክለብ በተመለከተ ሶኬር ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የሚዘግብበት መንገድ ሚዛናዊነት የጎደለ መሆኑን የዎላይታ ዲቻ ስፓርት ክለብ አስታወቀ።

ዎላይታ ድቻ የስም ለወጥ ሳያደርግ አድርጓል በሚል በሶኬር ኢትዮጵያና በእግርኳስ ፌደሬሽን የተሰራጨው ዜና ሀሰት መሆኑንም ክለቡ አስታውቋል።

ዎላይታ ድቻ ለ2015 ዓ.ም ጨዋታ ዘመን ለመጨዋት የሚያስችል ፈቃድ ያገኘውም የዎላይታ ድቻ ስፖርት ክለብ በሚል ስም መሆኑን የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ወንድሙ ሳሙኤል ማምሻውን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በስልክ ገልጸዋል።

ሶኬር ኢትዮጵያ ስለ ዎላይታ ዲቻ ክለብ በተመለከተ በተደጋጋሚ የሚዘግብበት መንገድ ሚዛናዊነት የጎደለ መሆኑም ከጊዜ ወደ ጊዜ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱንም ስራ አስኪያጁ አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ለዎላይታ ዲቻ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ክለቦች ያወጣው መመሪያ በተለየ መንገድ ለአንድ ክለብ ብቻ ተግባራዊ የሚሆንበት አካሄድ እንደማይኖም አቶ ወንድሙ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልጸዋል።

ሶኬር ኢትዮጵያ ስለ ዎላይታ ዲቻ ክለብ በተመለከተ ስያሜ ለውጥ አለመኖሩን በተለያዩ መገነኛ ዘዴዎች ማብራሪያ ብንሰጥም በዛሬው ዕለት ጭምር በደረጃ ሰንጠረዥ ላይ “ዎላይታ” የሚለውን ስም ለመጠራት መቸገሩን ቅሬታ አቶ ወንድሙ አቅርበዋል።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያም የእግር ኳስ ፌደሬሽን ዘገባና ሶከር ኢትዮጵያ ዘገባ ጠቅሰን ዘገባ መሰረታችን የሚታወስ ሲሆን በጉዳዩ ዙሪያ የኢትዮጵያ እግር ኳስን ማብራሪያ ለማግኘት ጠየቀን ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም።

ሶኬር ኢትዮጵያ ጋዜጠኛ ዳንኤል መስፍን ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ያውጡትን ዘገባ በተመለከተ “ዘገባውን የሰራነው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ዘገባ አይተን ነው የሰራነው፥ ከክለቡ በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ ስንገኝ ማስተካከያ እናደርጋለን” ብለዋል።

የእግርኳስ ፌደሬሽን የዎላይታ ዲቻ ክለብ የስም ለውጥ ሳያደርግ አድርጓል ያለበት በምን አግባብ እንደሆነ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ መረጃውን ካገኘ የሚያደርስ ይሆናል።