1664646264179

ከዚህ ቀደም ዎላይታ ድቻ ስፖርት ክለብ በሚል ስያሜ ይታወቅ የነበረው ክለብ ከዚህ በኋላ “ድቻ ስፖርት ክለብ” በሚል እንደሚጠራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በቅርቡ እንዳስታወቀው የብሔር እና ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸው ስያሜዎችን የሚጠቀሙ ክለቦች ስያሜያቸውን እንዲያስተካክሉ ባወጣው መመሪያ መሰረት ዎላይታ ድቻ ቀዳሚው ማስተካከያ ያደረገው ክለብ ሆኗል።

በዚህም መሠረት ከዚህ ቀደም “ዎላይታ ድቻ ስፖርት ክለብ” በሚል ይጠቀምበት የነበረውን መጠርያ ወደ “ድቻ ስፖርት ክለብ” ስለመለወጡ ክለቡ ለፌደሬሽኑ አሳውቋል።

በቀጣይ ሌሎች ክለቦችም ማስተካከያ ያደርጋሉ ተብሎም እንደሚጠበቅ ፌደሬሽኑ አያይዞም ገልጿል ስል ሶኬር ኢትዮጵያ ዘግቧል።

1 thought on “ሰበር ዜና |ዎላይታ ድቻ ስያሜው ላይ ማስተካከያ ማድረጉ ተገለፀ”

Comments are closed.