
Exif_JPEG_420

በናትናኤል ጌቾ ቤታሎ
በዎላይታ ሶዶ ከተማ በርካታ የቀበሌ ቤቶች በአቅመ ደካማ ወገኖች ይልቅ የግል ቤት ባላቸው ግለሰቦች በህገ ወጥ መንገድ እንደተያዙ ተነገረ።
በከተማዋ በርካታ የቀበሌ ቤቶች በቀድሞና በአሁኑ መንግስት አመራሮች፣ በዘመዶቻቸው፣ ቅርብ ሰዎችና በባለሃብቶች የተያዙ ሲሆን የመንግስት ሰራተኞችና አቅም የሌላቸው በቤት ክራይ በሚሰቃዩባት የቀበሌ ቤቶችን ለአመታት የሚጠቀሙ መኖራቸው ፍትሃዊ አለመሆኑም ቅሬታቸውን ለ”ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ” ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የግል ቤት እያላቸው፣ ቤት ለመስራት ሆነ ቤት ለመከራየት አቅም እያላቸው በመንግስት ቤቶች እየኖሩ ከአቅም ማነስ የተነሳ በከተማዋ ለሚቸገሩ ወገኖች በህጋዊ መንገድ በሌሎች ከተሞች እንደሚደረግ ሁሉ ተግባራዊ እንዲሆን የከተማዋ አስተዳደር የህግ የበላይነት ለማስከበር ህጋዊ እርምጃ የመውሰድ ኃላፊነት ልወጣ እንደሚገባም አስተያየት የሰሰጡ ነዋሪዎቹ አሳስበዋል።
ከህዝቡ እየቀረበ ያለው ቅሬታ ትክክል መሆኑን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የገለፁት የሶዶ ከተማ ማዘጋጃዊ ቤቶች የከተማ ልማትና አስተዳደር ባለሙያ አቶ ተሰፋዬ ታደሰ፥ የራሳቸውን መኖሪያ ቤት አከራይተው በመንግስት ቤት የሚኖሩ ሰዎች እንዳሉና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተናበቡ የማስተካከያ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ተናግረዋል።

በሶዶ ከተማ ከ1 ሺህ 7መቶ 59 በላይ የመንግሥት የቀበሌ ቤቶች መኖሩን የገለፁት ባለሙያው የቀበሌ ቤቶች በከተማዋ ላይ ለምን ለባለስልጣናትና ለባለስልጣናት ዘመድ ብቻ ሆነ? ለምን በሌሎች ከተሞች ተግባራዊ እንደሚሆን አቅም ለሌላቸው ለምን አይሰጥም ? በየአካባቢው የሚገኙ አንዳንድ የቀበሌ ቤቶች በዋና ዋና መንገዶች ላይ ለከተማ ውበት ማነቆ በሆኑ ቦታዎች ይገኛሉና ለዚህ ምን የታሰበ ነገር አለ? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ስሰጡ “ለእንቨስመንት ምቹ የሆኑ ቦታዎች ተለይቶ በህጉ መሠረት ማልማት ለሚችሉ ባለሀብቶች እየተሰጠ እንዲሁም ለልማት ተነሺ ለሆኑ ግለሰቦች ምትክ ቦታ እየተሰጠ ነው፣ አግባብ ባልሆነ መንገድ የተያዙ የቀበሌ ቤቶችን ለአቅመ ደካማ ለሆኑ ግለሰቦችና እንደአስፈላጊነቱ ልዩ ምክንያት ላላቸው ግለሰቦች የማስተላለፍ ስራ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመናበብ እየሰራን ነው” ብለዋል።

የቀበሌ ቤቶችን ላለመልቀቅ በሌላ ቦታ የሰሩትን ቤት በዘመድ አዝማድ ስም ማድረግ፣ የያዙትን የቀበሌ ቤቱን ላለመልቀቅ በሐሰት ጋብቻቸውን ለማፈረስ የሚሞክሩ፣ ወደ ግል ስም ለማዘዋወር ለማስመሰል የሚያደርጉት ሁኔታ እንደሚስተዋል መታዘባቸውን ባለሙያው አክለው ተናግረዋል፡፡

“ክራይ ሰብሳቢዎች ማስረጃ ለማፈን ጉልበት አላቸው፡፡ አንደኛ ጉልበታቸው ሃብት ነው፡፡ በህገወጥነት ያለ አግባብ ባካበቱት ገንዘብ ይጠቀማሉ፡፡ ሁለተኛው ጉልበታቸው ስልጣንነው፡፡ በርካታ ጉዳዮችን የሚያበላሹት ስልጣንን ያለአግባብ የሚጠቀሙ በመኖራቸው እንዲሁም የገነቡትን የግል ቤት በሌላ ሰው ስም ያደርጋሉ” በማለት ችግሩን ለመጋፈጥ የሁሉም ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ ይናገራሉ፡፡
በዎላይታ ታይምስ ሚዲያ