“በትምህርት ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ለጋስነት ሳይሆን የወደፊት ሕይወታችንን ለመገንባት የሚያስችል ኢንቨስትመንት መሆኑን ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ ገልጸዋል።

የቀድሞ የኢፈዴሪ ቀዳማዊት እመቤት እና የኃይለማርያምና ሮማን ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ የቻይና ገጠር ልማት ፋውንዴሽን(CFRD) በተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት የሦስተኛ ዓመት ምስረታ በዓል ላይ በመገኘት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ ትምህርት ላይ የሚደረግ ማንኛውም መዋዕለ ንዋይ የተሻለ ነገን ለመፍጠር የሚደረግ ጥረት እንጂ ለጋስነት አለመሆኑም እንዲህ ሲሉ አመላክተዋል “በትምህርት ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ለጋስነት አይደለም፣ ይልቁንም የተሻለውን ጥቅም የሚከፍል የወደፊት ሕይወታችንን ለመገንባት የሚያስችል ኢንቨስትመንት ነው።” ብለዋል።

በቀድሞ ስሙ የቻይና ፋውንዴሽን ለድህነት ቅነሳ (CFPA) በመባል የሚታወቀውና በአሁን መጠሪያው የቻይና ገጠር ልማት ፋውንዴሽን(CFRD) ከተሰኘው ግብረ ሰናይ ድርጅት እንዲሁም በአገር ውስጥ ከሚገኙ ከተለያዩ ተቋማት ሀብት በማሰባሰብ እ.ኤ.አ በ2014 በአዲስ አበባ ከተማ የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም በማስጀመር ተጨባጭ ለውጥ መስተዋል እንደቻለም ወይዘሮ ሮማን አስታውሰዋል።

አክለውም በአሁኑ ስዓት የኃይለማሪያምና ሮማን ፋውንዴሽን በአገሪቱ ገጠራማ የአርብቶ አደር አካባቢዎች ያስጀመራቸውን የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም እና ተያያዥነት ያላቸው ፕሮጀክቶች በመደገፍ የቻይና ገጠር ልማት ፋውንዴሽን(CFRD) ላሳየው አጋርነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የቻይና ገጠር ልማት ፋውንዴሽን ፕሬዝዳንት ዌንካይ ዠንግ በበኩላቸው ከኃይለማሪያምና ሮማን ፋውንዴሽን ጋር በቅንጅት በመሆን በርካታ ተግባራትን ፋውንዴሽናቸው እንደፈጸመና በዚህም ኃሮፋ የማስፈጸም አቅሙን እና ታማኝነቱን ያስመሰከረ ተቋም መሆኑን በመግለጽ በቀጣይ ጊዜያት የትብብር ማዕቀፉን በማስፋት በርካታ ጉዳዮች ላይ በትብብር እንደሚሰሩ ጠቁመዋል።

በስነ ስርዓቱ ላይ የኃይለማሪያምና ሮማን ፋውንዴሽን በፕሮጀክቶች አፈጻጸም ላበረከተው የላቀ አስተዋጻ ኦና ታማኝ አጋርነት ከቻይና ገጠር ልማት ፋውንዴሽን (CFRD) የእውቅና ሰርተፍኬት መሸለማቸውን ከፋዉንዴሽን ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: