
በአለም ላይ አሁን አሁን እየተበራከተ የመጣውን የሞባይል ስልኮቻችን አማካኝነት የሚፈጸሙ ማጭበርበሮችን ለመከላከል ምን ምን የጥንቃቄ አማራጮችን መተግበር ይኖርብናል?

• ለሞባይሎቻችን ጠንካራ የይለፍ-ቃል መጠቀም፣
• ስልኮቻችንን በማንጠቀምበት ጊዜ መቆለፍ መቻል ፤
• ሚስጥራዊ የሆኑ የግል ወይም የድርጅት መረጃዎችን ለምሳሌ የይለፍ-ቃል፣ የአካዉንት ቁጥር፣ ኢ-ሜይል መረጃና ሌሎችን ዶክመንቶችን ሞባይል ስልካችን ላይ አለማስቀመጥ፤
• ከማናቃቸዉ የተለያዩ ምንጮች የሚለቀቁ ሶፍትዌሮችና አፕሊኬሽኖችን አለማውረድና አለመጫን ፤
• በሞባይላችን የምናያቸዉንና የምንጠቀምባቸዉን ድረ-ገጾች “URL” በጥንቃቄ ማየትና መለየት መቻል፤
• በማናቀዉ የሞባይል ቁጥር በሚደወልበት ጊዜ ምላሽ አለመስጠት፤
• ለማንኛዉም ዶክመንቶች/ ፋይሎች በይለፍ-ቃል ወይም በኮድ መቆለፍ መቻል ፤
• እንዲሁም ማንኛዉንም የይለፍ-ቃል በየጊዜዉ መቀያየር ተገቢ ነዉ፡፡ ከINSA የተወሰደ