በቦክስ ስፓርት ከ62 በላይ ወርቅ ተሸላሚ የሆነች ብርቱዋ ሴት ከዎላይታ-ኢትዮጵያ እስከ አለምአቀፍ መድረክ

ቤተል ወልዴ ትባላለች፦ ውልደትና ዕድገቷ ዎላይታ ሶዶ ነው፥ በቦክስ ስፓርት የተመሰከረላት ወጣት ናት፣ አብዛኞቹን ተጋጣሚዎችን በበቃኝ ማሸነፏ ደግሞ ለየት ያደርጋታል፤ እስከአሁን ድረስ ባደረገችው በቦክስ፣ በኪክ ቦክስና ሞይንታይ ውድድሮች አሸናፊ በመሆን 63 ሜዳሊያዎች ባለቤት ናት። ለየት የሚያደርገው ደግሞ ከእነዚህ ሜዳሊያዎች አንዱ ብቻ የነሀስ ሲሆን ሌሎች በሙሉ የወርቅ ብቻ መሆኑንም ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አረጋግጣለች።

ከዓመታት በፊት ዎላይታ ዞንን ወክላ በክልልና በአገርአቀፍ ደረጃ በሴቶች ቦክስ ስፖርት ሻምፒዮን በመሆን ትታወቃለች።

ቀጥሎ ባሉ ጊዜያት ለአካዳሚ፣ ለኒያላና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ስፖርት ክለብ በመጫወትም በርካቶችን በበላይነት በማሸነፍ እንዲሁም የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት በመሆን እውቅና ያተረፈች እንቁ ወጣት ናት።

በቅርቡ መስከረም ወር 2015 ዓ.ም ኢትዮጵያን ወክላ በተሳተፈችበት የሞይንታይ ኢንተርናሽናል ውድድር የቤላሩሱዋን ተወዳዳሪ በበላይነት አሸንፋ የሀገሯን ስም ከፍ አድርጋ አስጠርታለች።

ከወራት በኋላ ደግሞ የኢትዮጵያ ሰንደቅ-ዓላማ ይዛ ለመልስ ውድድር ወደ ቤላሩስ ለመሄድ የቀጠሮ ቀናቶችን እየጠበቀች እንደሆነም ተናግራለች።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

%d bloggers like this: